2 months ago
የጉበት መስባት ምን ማለት ነው?
✍ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት በጉበት ላይ ሲኖር የጉበት መስባት(Fatty Liver) ይባላል። ትንሽ መጠን ያለው የስብ ክምችት እንደ ችግር አይቆጠርም።
✔️እንደሚታወቀው ጉበት ከሰውነታችን አካል ክፍሎች በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲሆን በምግብና መጠጥ አማካኝነት ወደ ሰውነታችን የገቡ ነገሮችን በማጣራትና በመፈተሽ ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድና የጉዳት መጠናቸውን በመቀነስ ሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችልን ከባድ ችግር ያስቀራል።
✔️መጠኑ የጨመረ የስብ መጠን ለጉበት መጠቃትና መመረዝ ያጋልጣል። ይህም ጉበት ላይ ጠባሳ እንድፈጠር ያደርጋል። ይህ ደግሞ ጉበት ስራውን በአግባቡ እንዳያከናውን ያደርገዋል።
✅በጉበት ውስጥ ስብ ሲከማች ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች
👉 የጉበት ጠባሳ መፈጠር
#የጉበት ጠባሳ ካለ የሚታዩ ምልክቶች
1. የክብደት መቀነስና ድካም ስሜት
2. በአፍንጫ ደም መፍሰስ
3. የቆዳ ማሳከክ
4. ቆዳና አይን ቢጫ መሆን
5. የሆድ ህመም
6. የሆድ ማበጥ
7. የእግር ማበጥ
8. ግራ መጋባት
#በጉበት ላይ ለምን ስብ ይጠራቀማል?
👉ብዙ ጣፋጭ ተጠቃሚ መሆን
👉መጠኑ ከፍ ያለ አልኮል መጠጣት
ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮች
👉 ውፍረት
👉 ከፍተኛ ደም ግፊት
👉ስኳር በሽታ
👉ብዙ ስብ በሰውነት ውስጥ መከማቸት
👉የጉበት ቫይረስ ሲ
👉መድሀኒቶች(methotrexate, tamoxifen, amiodorone and valproic)
👉ለመርዛማ ነገሮች መጋለጥ
👉እርግዝናና ሌሎችም ናቸው።
መመርመሪያ መንገዶች
👉የተለያዩ ጥያቄዎች በመጠየቅ
👉የተለያዩ ምልክቶችን በማየት
👉የደም ናሙና በመውሰድ
👉ከጉበት ናሙና በመውሰድ
ህክምናው
👉የሚታዘዝ መድሀኒት ባይኖርም አልኮልን ባለመጠጣት፡ ክብደትን በመቀነስና የባለሙያ ምክርንና ክትትልን በማክበር መቀነስና ከችግሩ መላቀቅ ይቻላል።
seledadotio

7 months ago
የታሸጉ ምግቦች አያዘውትሩ‼️
" በአሁኑ ሰአት ከወጣቶች በዘለለ እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የስኳር እና የጨው ይዘት ያላቸው የታሸጉ ምግቦች ናቸው " - የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር
ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ ተዘጋጅቷል።
አዋጁ መዘጋጀቱን ተከትሎ ፦
- የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጭ ማህበራት ህብረት (CORHA)፣
- የኢትዮጵያ የልብ ማህበር፣
- የኢትዮጵያ የስኳር በሽታ ማህበር እና የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር በጋራ በመሆን ከቀናት በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም አበራ " በአሁኑ ሰአት ከወጣቶች በዘለለ እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው " ብለዋል።
" ለኩላሊት በሽታዎች ዋነኛ ምክንያቱ የስኳር እና የጨው ይዘት ያላቸው የታሸጉ ምግቦች ናቸው " ሲሉም ገልፀዋል።
አቶ ቢኒያም አበራ በዝርዝር ምን አሉ ?
" በማህበራችን ውስጥ አብዛኛው ኩላሊታቸው የተጎዱ ሰዎች ለኩላሊታቸው መጎዳት ዋነኛ ምክንያት የሆነው ደም ግፊት እና የስኳር በሽታዎች ናቸው። እነዚህ በሽታዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከአመጋገብ ስርአት ጋር የተገናኙ ናቸው። ምክንያቱም የታሸጉ ምግቦች በአብዛኛው የስኳር እና የጨው ይዘት አላቸው።
በተለይ ደግሞ በፋብሪካ የሚቀነባበሩ ምግቦች በውስጣቸው በምግብ ማቀነባበር ስርአት ውስጥ የተጠራቀመ የስብ ክምችት አለ። ይህ የሚጨመር ስኳር ሰዎች በሚመገቡበት ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲገባ ያደርጋል። ይህ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያዛባዋል፤ በዚህም የስኳር በሽታ እንዲከሰት ያደርጋል። በምግብ ውስጥ የሚጨመር ንጥረ ነገር ደግሞ የደም ግፊትን ያመጣል። በመሆኑም ኩላሊት ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ ያዳክሙታል። በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ኩላሊት ስራውን እንዳይሰራ ያደርጋል።
እነዚህ ነገሮች በተናጠልም ሆነ በድምር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች እያጠቁ ያሉ ንጥረ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ እነዚህን ንጥረ ነገሮች ወደ ዜጎች በሚመጡበት ጊዜ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል።
በታሸጉ ምግቦች ሽፋን ላይ በውስጣቸው የያዙት ንጥረ ነገር በአይነት እና በመጠን ሊገለጽ እንዲሁም ሰዎች እነዚህን ሲመገቡ ሊደርስባቸው የሚችሉ ጉዳቶች በመሸፈኛቸው ላይ በጉልህ መቀመጥ አለባቸው።
በታሸጉ ምግቦች ላይ በቂ ቁጥጥርና ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።
እነዚህ ምግቦች በማህበረሰባችን ላይ እያደረሱት ያለው ጉዳት እና ቀውስ ለመቀነስ ማህበራችን ይህ አዋጅ ቶሎ ተፈጻሚ እንዲሆን ይሰራል " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግብ ህክምና ባለሙያ እና የኢትዮጵያ ስነ ምግብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ዘላለም ከበደ " ኢትዮጵያ በፋብሪካ በተቀነባበሩ እና ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት ለሚደርሱ የጤና ጉዳቶች በየዓመቱ ከ31 ቢሊየን ብር በላይ ታወጣለች " ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም " በየስአቱ 25 ሰው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ማለትም በስኳር፣ በኩላሊት፣ በጉበት እና በልብ እንዲሁም በደም ቧንቧ በሽታዎች ይሞታሉ፣ በአሁኑ ስአት የህመሙ ጫና ከ52 በመቶ በላይ ሆኗል " ነው ያሉት።
" የምግብ ጥራትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በርካታ ሰዎች የታሸጉ ምግቦች ጥሩ እየመሰሏቸው ሲገዙ ይታያል። ይህ በጥናት መረጋገጥ አለበት። ማህበረሰቡ ባለው የግንዛቤ ክፍተት ምክንያት እየተጠቀመ እየተጎዳ ነው " ብለዋል።
" ማህበረሰቡ በአዋጁ መሰረት ክልከላ የሚደረግባቸው የስብ፣ የስኳር እና የጨው መጠናቸውን ያልጻፉ የታሸጉ ምግቦችን ሲያዩ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ አለባቸው። አዋጁ ቶሎ ወደ ተግባር ገብቶ ክፍተቶቹ እየታዩ መስተካከያ ሊደረግበት ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።ቲክቫህ

9 months ago
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የጉበት ንቅለ ተከላን ለማስጀመር ቅድመዝግጅት እያረገ መሆኑን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ በጉበት ህመም የሚጠቁ ዜጎች በርካታ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ከኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ የሚመጣ የጉበት ህመም በስፋት እንደሚስተዋል ተነግራል።
በተለይም ደግሞ እንደ ሀገር ሄፓታይተስ ቢ የተባለው የጉበት በሽታ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ በህክምና ኮሌጁ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ንዋይ ፀጋዬ ለብስራት ሬድዮ የተናገሩ ሲሆን በዚሁ በሽታ የሚያዙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሆስፒታሉ የጉበት ንቅለ ተከላ አገልግሎትን ከአመት በኋላ ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ሕክምናው እንዲጀመር ለማድረግ ለኮሌጁ የጉበት ሕክምና ስፔሻሊስቶች ፣ ለጉበት ቀዶ ሕክምና ሐኪሞች እንዲሁም ነርሶች ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ባለሙያዎች በውጪ ሀገር ጭምር ስልጠናዎችን የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቶላቸዋል ሲሉ የገለፁ ሲሆን ይህም የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምናውን ለመስጠት መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።
የጉበት ንቅለ ተከላው ህክምና ሲጀምር በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅን የመጀመሪያው የጉበት ንቅለ ተከላ ሕክምናን የሚሰጥ ይሆናልም ሲሉ አቶ ነዋይ ጨምረው ገልፀዋል።
ለዜጎች ህልፈት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ የጉበት በሽታ በመሆኑ የዜጎችን ህይወት ለማትረፍ የህክምና አገልግሎቱ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሏል ሲል ብስራት ኤፍ ኤም ዘግቧል ።

10 months ago
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና በቅርቡ ይካሄዳል
#ethiopia | ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምናበቅርቡ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ንዋይ ፀጋዬ፥ የሆስፒታሉ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ልዑክ በጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ከፍተኛ ልምድ ባለው የካሊፎርኒያው ፓሲፊክ የህክምና ማዕከል ለሳምንታት የቆየ የምልከታስልጠና ሲያደርግ መቆየቱን ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።
በትውልደ አትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት የጉበት ንቅለ ተከላ የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ቅድስት ኪዳነ ይልማ አመቻችነት የተካሄደው መርሐ ግብር፥ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የጉበት ንቅለ ተከላ አገልግሎት ለማከናወን በምታደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለውታል።
የባለሙያዎች ቡድን አባላቱ በርካታ የጉበት ንቅለ ተከላ ሂደቶችን የተመለከቱ ሲሆን ከዋነኛ የንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገናሐኪሞች የተግባር ስልጠና እና የዕለት ተዕለት ምክር ማግኘታቸውንም ነው የተናገሩት።
ቡድኑ በቆይታው ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች የጤና ደረጃ፣ የለጋሾች ልየታ እና በህክምናው ዙሪያ ያሉትን ስርዓቶች በተመለከተ አስፈላጊ እውቀት ማግኘቱን ጠቁመዋል።
ሆስፒታሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በበቂ ዝግጅት ወደ ሥራ ሲገባ ለጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ውጭ ሀገር መሄድን እንደሚያስቀርአመላክተዋል።
በርናባስ ተስፋዬ

Sponsored by
Surafel
11 months ago
ዓለም እንደሚያውቃት የማታውቀው ሳርባት ጉላ
#ethiopia | ሳርባት ጉላ የተወለደችው በአፍጋኒስታን ቢሆንም በልጅነቷ በመሰደድ በፓኪስታን የመጠለያ ካምፕ ውስጥ መኖር ትጀምራለች፡፡
በአንድ ቀንም ወድ ትምህርት ቤት እየሄደች አንድ የውጪ ዜጋ ፎቶ ለማንሳት ጥያቄ ያቀርብላታል፡፡ ሳርባት በጊዜው የ13 ዓመት ታዳጊ ነበረች፡፡
እሷም ፈቃደኛ ሆና ፎቶውን ተነሳች፡፡ ሳርባት በመጀመሪያ ፊቷን ሸፍና መነሳት ብትመርጥም በፎቶ አንሽው ጎትጓችነት ፊቷን ገልጣ መነሳት ጀመረች ፡፡
ፎቶ አንሺው ስቲቭ ማኬሪ ይባላል፡፡ የናሺናል ጂኦግራፊ ፎቶግራፈር ነው፡፡
ያንን ፎቶ አንስቶ ወደ ሃገሩ በመመለስ በትልቁ አሳትሞ ለህዝብ አቀረበው፡፡
በዚህም ስቲቭ ብዙ ገንዘብና ዓለም አቀፍ ዝናንን ማግኘት ቻለ፡፡
ሳርባት ግን ፎቶዋን ያነሳትን ሰውም ሆነ ፎቶዋ ዓለም ላይ እውቅና እንዳገኘ የምታውቀው ገነር አልነበረም፡፡
ከዛም ሳርባት ወደ ትውልድ ሀገሯ አፍጋኒስታን በመመለስ ትዳር መስርታ አምስት ልጆችን ወልዳ ህይወቷን ቀጠለች፡፡
እ.ኤ.አ በ2002 ስቲቭ ሳርባትን በድጋሚ ለማየት ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ወደ አፍጋኒስታን አቅንቶ ሌላ ፎቶ አንስቷት ተመለሰ፡፡
ከዛ ግን የሳርባት ህይወት መመሰቃቀል ጀመረ፡፡ ባለቤቷ በጉበት በሽታ ሞቶባት ስለነበር ብቻዋን ኑሮ መግፋት አቅቷት ድጋሚ ወደ ፓኪስታን ከልጆቿ ጋር ተሰደደች፡፡
ነገር ግን በህገወጥ መንገድ ድንበር በመሻገሯ በፓኪስታን መንግስት ታሰረች፡፡ መታሰሯም በምዕራባውያን ዘንድ መነጋገሪያ ርዕስ ነበር፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ፎቶውን ያነሳትም ሆነ ናሺናል ጂኦግራፊ እሷን ለመርዳት ምንም አይነት ጥረት አላደረጉም፡፡
የምዕራባውያኑን ስሜት የተረዳው የአፍጋኒስታን መንግስት ወደ ሃገሯ እንድትመለስ በማድረግ ቤት ሰጥቷን እንድትኖር አደረገ፡፡
በዛ ጊዜ ነበር ሳርባት ደህንነቷ የተጠበቀ እንደሆነ አስባ መኖር የጀመረችው፡፡ ሆኖም ብዙ ሳይቆይ ታሊባን አፍጋኒስታንን መቆጣጠሩን ተከትሎ ሳርባት መልሳ አደጋ ውስጥ ገባች፡፡
የታሊባን አባላትን እሷንና እንደሷ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ላይ ጥቃት ያደርሱ ጀመር፡፡
ከዛም ስቲቭ እና የስራ ባልደረቦቹ ሳርባት ደህንነቷ እንዲጠበቅ ሲሉ ጽሁፎችን ማውጣት ጀመሩ፡፡
ይህ ግን ሊሰራ አልቻለም ነበር፡፡ በመጨረሻም ሳርባት ወደ ጣልያን ሀገር ገባች፡፡
አሁን ላይ ሳርባት ህይወቷን በጣልያን እየገፋች ሲሆን በ2022 ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ የተነሳውት ፎቶ በርካታ ችግሮች ይዞብኝ መጥቷል፡፡
ያንን ቀን በደንብ አስታውሰዋለው ፎቶውን ባልነሳው ምርጫዬ ነበር ስትል ተናግራለች፡፡
በዳግማዊት አበበ

Comments