በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የጉበት ንቅለ ተከላን ለማስጀመር ቅድመዝግጅት እያረገ መሆኑን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ በጉበት ህመም የሚጠቁ ዜጎች በርካታ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ከኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ የሚመጣ የጉበት ህመም በስፋት እንደሚስተዋል ተነግራል።
በተለይም ደግሞ እንደ ሀገር ሄፓታይተስ ቢ የተባለው የጉበት በሽታ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑ በህክምና ኮሌጁ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ንዋይ ፀጋዬ ለብስራት ሬድዮ የተናገሩ ሲሆን በዚሁ በሽታ የሚያዙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሆስፒታሉ የጉበት ንቅለ ተከላ አገልግሎትን ከአመት በኋላ ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ሕክምናው እንዲጀመር ለማድረግ ለኮሌጁ የጉበት ሕክምና ስፔሻሊስቶች ፣ ለጉበት ቀዶ ሕክምና ሐኪሞች እንዲሁም ነርሶች ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ባለሙያዎች በውጪ ሀገር ጭምር ስልጠናዎችን የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቶላቸዋል ሲሉ የገለፁ ሲሆን ይህም የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምናውን ለመስጠት መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።
የጉበት ንቅለ ተከላው ህክምና ሲጀምር በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅን የመጀመሪያው የጉበት ንቅለ ተከላ ሕክምናን የሚሰጥ ይሆናልም ሲሉ አቶ ነዋይ ጨምረው ገልፀዋል።
ለዜጎች ህልፈት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ የጉበት በሽታ በመሆኑ የዜጎችን ህይወት ለማትረፍ የህክምና አገልግሎቱ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሏል ሲል ብስራት ኤፍ ኤም ዘግቧል ።

9 months ago