2 months ago
ማርከስ ራሽፎርድ ወደ እናትቤቱ
#ethiopia | እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በባርሴሎና ቤት የነበረውን የውሰት ዘመን አጠናቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ዮናይትድ ለመመለስ ተቃርቧል።
ተጫዋቹ በካምፕ ኑ ስኬታማ የውሰት ጊዜን ቢያሳልፍም፣ ከብሉግራናዎቹ ጋር የሚኖረው ቆይታ በዚህ ክረምት እንደሚያበቃ ተረጋግጧል።
የባርሴሎና አመራሮች ተጫዋቹን በ30 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ በቋሚነት የመግዛት ፍላጎት እንደሌላቸው ለኦልድትራፎርዱ ክለብ በይፋ አስታውቀዋል።
የራሽፎርድ የውሰት ውል በዚህ ወር መጨረሻ ላይ የሚያበቃ ሲሆን፣ ከሰኔ 30 ጀምሮ በይፋ የማንችስተር ዮናይትድ ተጫዋች ሆኖ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዴኮ ራሽፎርድ በክለቡ መልካም ጊዜን እንዳሳለፈ ገልጾ፣ ሆኖም ዮናይትዶች የጠየቁት የዝውውር ዋጋ ክለቡ ካቀደው በጀት በላይ መሆኑን አረጋግጧል።
ካታላኖቹ ተጫዋቹን በድጋሚ በውሰት ውል ለማቆየት ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ የማንችስተር ዮናይትድ አቋም ካልተቀየረ ግን የ28 ዓመቱ አጥቂ ወደ እንግሊዝ የመመለሱ ነገር በእጅጉ አይቀሬ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ማርከስ_ራሽፎርድ #ማንችስተር_ዮናይትድ #ባርሴሎና #የተጫዋቾች_ዝውውር #የስፖርት_ዜና

Comments