22 days ago
ማስታወቂያ
*******
የአዲስ ዓመት የብርሃን ስጦታ፦ የአይን ብሌንዎን ለመለገስ ቃል ይግቡ!
አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ጅምርና አዲስ ብርሃን ይዞ ይመጣል። በዚህ አዲስ ዓመት ከምናበረክታቸው ስጦታዎች ሁሉ የሚበልጠውና ዘላለማዊ ህያውነት ያለው ስጦታ አንዱን ሰው ከጨለማ ወደ ብርሃን ማውጣት ነው።
በሃገራችን በርካታ ወገኖቻችን በአይን ብሌን ሕመም ምክንያት የቀኑን ብርሃን፣ የወዳጆቻቸውን ፈገግታና የአለምን ውበት ማየት ተስኗቸዋል። ለእነሱ ትልቁ የአዲስ ዓመት ምኞትና ስጦታ ደግሞ ማየት ነው!
በዚህ አዲስ ዓመት የእርስዎን የአይን ብሌን ለመለገስ ቃል በመግባት ለአንድ ወገን የማይጠፋ የብርሃን ስጦታ ያበርክቱ።
ዛሬውኑ ይመዝገቡ፤ የሌሎች ብርሃን ይሁኑ!
መልካም አዲስ ዓመት!

24 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) እንኳን ለ2019 ዓ.ም የሐዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አዲሱን ዓመት ለመቀበል በሆሳዕና ከተማ በተሰናዳው ልዩ መርሃ-ግብር፣ የሐዲያ ልጃገረዶች ባህልን፣ ጸጋን እና ተፈጥሯዊ ቁንጅናን አዋህደው ባቀረቡት የ"ያሆዴ ፋሽን ሾው እና የቁንጅና ውድድር" የከተማዋን ድባብ በልዩ ድምቀት አሸብርቀውታል።
በመድረኩ ላይ በኩራት የተራመዱት እነዚህ ቆነጃጅት የለበሱት ያሸበረቀ ሀገረሰባዊ አልባሳት፣ የዘመኑን መታደስ ብቻ ሳይሆን የሐዲያን ሕዝብ የረጅም ዘመን የማንነት ውበት እና የጥበብ ከፍታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነበር። ባህል ከዘመን ጋር ሲራመድ፣ ውበትም ከማንነት ጋር ሲዋሃድ ምንኛ ያምራል!
መልካም አዲስ ዓመት! የያሆዴ በዓል የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት ዘመን ይሁንልን! 🌼

Sponsored by
Surafel
29 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት| የአምናዋ ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሐሤት ደረጀ የአዲስ ዓመት መልዕክቷ እንዲህ ይነበባል፦ "በራሳችን የዘመን ቀመር አዲስ ምዕራፍን ዳግም መጀመር ልዩ የሆነ የውበት ስሜት አለው። አዲሱን ዓመት በደስታ ስንቀበል፣ ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝ ትልቅ ምኞት፤ ሰላም፣ እውነተኛ ፈውስ እና በአንድነት የምንፈነድቅባቸው በርካታ ምክንያቶች እንዲበዙላት ነው።
"አዲሱ 2019 ዓ.ም ሩህሩህ ቀናትን፣ ለወጣቶቻችን ሰፊ ዕድሎችን፣ እንዲሁም እያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ብሩህ ተስፋን ይዞልን ይምጣ።
ይህንን መልእክቴን ለምታነቡት ደግሞ፤ ለሰዎች የምታካፍሉት ጣፋጭ የምሥራች፣ አብረዋችሁ ደስታችሁን የሚያከብሩ ቅን ሰዎች፣ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ስታልሙት የነበረውን ህልም እውን ለማድረግ የሚያስችል ወኔና ድፍረት ይስጣችሁ። ቆም ብላችሁ፣ "አምላኬ ሆይ... ለዚህች ቀን እኮ ነበር ስጸልይ የነበረው" ብላችሁ በደስታ የምታመሰግኑባቸው ልዩ አጋጣሚዎች በዓመቱ ውስጥ ይብዙላችሁ።
ከብዙ ፍቅር ጋር፣ መልካም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት!
መልካም አዲስ ዓመት! 🤍🌼 እንቁጣጣሽ!

30 days ago
መልካም አዲስ ዓመት።
በጎጆ የህሙማን ማረፊያ የበጎ ፍቃደኝነት ጉብኝት እንደቀጠለ ነው...
እንደተለመደው የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫን (የእንቁጣጣሽ) በዓልን በማስመልከት የዘወትር የማረፊያው ቤተሰብ ቤሩት(መሠረት) እና ቤተሰቦቿ የሙስሊም እና የክርስቲያን በጎችን በመግዛት በህሙማኑ ማረፊያ በመገኝት በዓሉን በማዘጋጀት፣ አቶ ፍቃዱ ጣፋ እና ቤተሰቦቹ 240 እንቁላል ለበዓሉ በማበርከት እንዲሁም ትጉ እና ባለቤቷ ለመቶ ሰው የሚሆን የሙስሊም እና የክርስቲያን ምግብ,በማቅረብ፣ የቡና ሴሬሞኒምውን በማዘጋጀት ከህሙማኑ ጋር በዓሉን በዚህ ሁኔታ አሳልፈዋል።
ቤሩት(መሠረት)ን እና ቤተሰቦቿን፣ ትጉ እና ባለቤቷን እንዲሁም አቶ ፍቃዱ ጣፋ እና ቤተሰቦቹን እያመሰገንን መላው የማረፊያው ቤተሰብን መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላቹ እንላለን።
የማረፊያው ተጠቃሚ ህሙማንን እንዲሁም ሌሎችም ወገኖች በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ባለንበት እንኑር እንላለን።

1 month ago
☎️+971527866251
የዳንዩብ ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር፣ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ቀዳሚ የሪል እስቴት አልሚዎች አንዱ የሆነውን ዳንዩብን የሚመሩት አቶ ሪዝዋን ሳጃን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለደንበኞችና ለአጋሮች የአዲስ ዓመት ሰላምታቸውን አቅርበዋል።
አዲሱ ዓመት ሰላም፣ ጤና፣ ደስታ፣ ብልጽግና እና ስኬት ይዞላችሁ ይምጣ። 🙏✨
እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! 🎉
— Brook Real Estate 🏙️🏡
#brookrealestate #danube #rizwansajan #መልካምአዲስዓመት #እንቁጣጣሽ #ኢትዮጵያ #ዱባይ #ሪልእስቴት #ethiopiannewyear
1 month ago
ከጎረቤት አልፎ ወደ ሀገር የዘለቀው የኢትዮጵያውያን የማጋራትና የደግነት እሴት
**************
መስከረም ሲጠባና አደይ አበባ የኮረብታዎችን ማዕረግ ለብሶ ሲያብብ፣ ህፃናት በውብ ባህላዊ አልባሳታቸው አምረው "አበባ አየሽ ወይ፣ ለምለም" እያሉ በየደጃፉ በእንቁጣጣሽ ዝማሬ አዲሱን መንፈስ ያበስራሉ።
አባወራዎች የሸማኔውን ጋቢ ተጎናጽፈው፣ እናቶች በባህል ቀሚስ ተውበው፣ መላው ቤተሰብ ማዕድ በጋራ ታድመው በዓሉን በደስታ ያደምቁታል።
አዲስ ዓመት በሀገራችን የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፤ ዘመድ ከዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ያለው ለሌለው እጁን ዘርግቶ የሚያካፍልበት እና የደግነት እሴታችን የሚንጸባረቅበት ታላቅ ማኅበራዊ ሁነት ነው።
በኢትዮጵያውያን ባህል "ለብቻ መብላት" ነውር ተደርጎ ይታያል። ይህ የደግነት እሴት በተለይ በበዓላት ወቅት ከቤት አልፎ ወደ እምነት ተቋማትና የሕዝብ አደባባዮች ዘልቆ ይስተዋላል።
በየቤተእምነቱ ደጅ እና በየአደባባዩ አቅም የሌላቸውና ጧሪ አልባ ወገኖች እንዲሁም መንገደኞች በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማዕድ ይላክላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ይህ ማዕድ በማጋራት አብሮ የመደሰት እሴት ከቤተሰብ፣ ከጎረቤትና ከአካባቢ አልፎ ወደ ሀገር ደረጃ በመሻገሩ ፍቅርን እና መተማመንን በማጠናከር ላይ ይገኛል።
አዲሱ ዓመት የማካፈል ደግነታችን፣ የገበታ አብሮነታችንና ትስስራችን ተጠናክሮ ሀገራዊ መግባባት የሰፈነበት እንዲሆን እንመኛለን።
መልካም አዲስ ዓመት!
በልዩ እሸቱ
#ethiopia #newyear #ethiopiannewyear #sharing #ebc

የብሩህ ዘመን መባቻ፡- ከተፈጥሮ ጋር ተናብቦ ተስፋን የሚያድሰው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት
******************
የዘመን መለወጫ ለኢትዮጵያውያን በቀን መቁጠሪያ ላይ ከሚሰፍር የቁጥር ሽግግር የዘለለ እጅግ ጥልቅ ትርጉም አለው።
የክረምቱ ከባድ ደመና ተገፍፎ በጠራው የመስከረም ሰማይ ሲተካ፣ ካለፈው የውጣ ውረድ ትዝታ ተላቅቀን በአዲስ መንፈስ እና በጽኑ ዓላማ ወደፊት የምንራመድበት ታላቅ የሕይወት ምዕራፍ ይከፈታል።
አሮጌውን ዓመት በክረምቱ ጭጋግ ሸኝተን አዲሱን ዘመን በብራ ብርሃን ዛሬ ስንቀበል በልባችን ውስጥ የሚፈጠረውን ነገን የማለም ስሜት እና የታደሰ ሥነ-ልቦና ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ ነው።
መስከረም ሲጠባ ምድራችን በክት ልብስ እንዳጌጠች ውብ ኮረዳ ቢጫ ቀሚሷን ትለብሳለች። የደፈረሱ ወንዞች ሲጠሩ፣ ሰማዩ በብርሃን ሲደምቅ፣ ከዐደይ አበባ መፍካት ጋር መስኩ ሁሉ ውበት ሲላበስ የተፈጥሮን የዕይታ ድግስ ብቻ ሳይሆን የልብ መረጋጋትንም አብረን እንቋደሳለን።
ወራት ተቆጥረው አዲሱ ዓመት ሲመጣ ከሰማዩ እና ከወንዞቹ መጥራት ጋር ተያይዞ የሚያመነጨው መንፈስን የማደስ ኃይል መጪው ጊዜ ብሩህ እና ሰላማዊ መሆኑን የሚያበስር ሕያው የተፈጥሮ ምስክር ነው።
ይህ የተፈጥሮ እና የሰው ልጅ ውብ የዘመን መተካካት ከዕይታም ባለፈ ሌላ ትልቅ የሕይወት ፍልስፍናን ያወርሰናል።
ወቅቱ በክረምቱ ዝናብ፣ ብርድ እና ጭቃ ሳይበገሩ ያፈሰሱት ላብ እና የዘሩት ዘር ወደ ተስፋ ፍሬ የሚሸጋገርበት የሽልማት ጊዜ ነው።
በጭቃ እና በድካም ውስጥ የተዘራው ፍሬ በቅሎ እና አሽቶ የድካምን ዋጋ ሲያስገኝ፣ ተፈጥሮ ራሷ ትዕግሥትን፣ አይበገሬነትን እና ከማንኛውም ፈተና በኋላ ብርሃን መኖሩን በተግባር ታስተምረናለች።
ይህ የትጋት ውጤት እያንዳንዱ የሕይወት ፈተና ወደሚያብብ የተስፋ ፍሬ እንደሚቀየር የሚያረጋግጥልን ጽኑ ቃል ኪዳን ነው።
እነሆ አዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋን ሰንቆ መጥቷል! ይህ ዛሬ የተቀበልነው አዲስ ምዕራፍ የጀመርነው መልካም ጥረት ሁሉ የሚያብብበት፣ የምንመኘው ሰላም፣ መከባበር እና ወንድማማችነት ልክ እንደ ዐደይ አበባ ፈክቶ የሚታይበት እንዲሆን እንመኛለን።
አዲሱን የተፈጥሮ ብሩህነት ወደ ሕይወታችን አጋብተን፣ ይህን የታደሰ ተስፋ ሰንቀን በአዲስ መንፈስ ወደተሻለ የጋራ ከፍታ በፅናት እንጓዝ።
እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! መልካም አዲስ ዓመት!
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #ethiopiannewyear #enkutatash #newhope #brightfuture

ቅርጫ ከ 15 ሺሕ ብር ጀምሮ
🌼 ምዘገባ ሊጠናቀቅ ነው!
በተለመደው ጥራት እና ፈጣን አገልግሎታችን ለአዲሱ ዓመት የተዘጋጁ የቅርጫ መደቦች ሊያልቁ ነው።
⚠️ ጥቂት መደቦች ብቻ ቀርተዋል።
ከ 15 ሺሕ ብር ጀምሮ የተዘጋጁ መደቦችን ለማግኘት
📲 አሁኑኑ ይዘዙ!
📞 ስልክ፦ 09-20-80-98-21 / 09-20-72-91-52
📍 አጋፔ ኦንላይን ቅርጫ
💛 መልካም አዲስ ዓመት 💛

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ማን ምን አለ?
#ethiopia | የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የውጭ ሀገራት መሪዎች የዲፕሎማቲክ መሪዎችና እና አምባሳደሮች የመልካም ምኞት መልእክት አስተላልፈዋል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለአዲሱ ዓመት ባስተላለፉት የአዲስ አመት መልእክት ለኢትዮጵያውያን እና አውስትራሊያውያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አዲሱ አመት የሰላም የብልጽግና እና የደስታ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።
በተመሳሳይ የአውስትራሊያ የተቃዋሚ መሪ የሆኑት አንገስ ቴለር በበኩላቸው እንኳን ለ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኤመሰበርገር
አውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጎን እንዳለ በመግለፅ የሰላምና የደስታ ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።
የካሜሩን አምባሳደር ኤዉምቡዌ ሞኖኖ አዲሱ ዓመት የተስፋ እና የእድገት እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሴ የዕንቁጣጣሽ እና የእስራኤል "ሮሽ ሀሻናህ" አዲስ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት መዋላቸውን በመጥቀስ "መልካም አዲስ ዓመት ዕንቁጣጣሽ" ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) አምባሳደር አብደላ ሀሰን አልሻምሲ
የሀገራቸውን እና የኢትዮጵያን ጠንካራ ወዳጅነት በማንሳት የሰላምና የፍቅር ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።
የጀርመን፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስሪላንካ፣ የየመን እና ማሌዥያ ዲፕሎማቶች እና ኤምባሲዎችም በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #ethiopiannewyear #enkutatash #ethiopia #newyear2019 #peaceandunity #diplomacy

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
ውድ የፋስት መረጃ ተከታታዮች፡
በቅድሚያ ለነበረን አብሮነት፣ ለሰጣችሁን እምነትና ድጋፍ እጅግ አድርገን እንመርቃችኋለን። አዲሱ ዓመት፦
ሁላችሁም በየሙያችሁና በየሥራችሁ ስኬትን የምታጭዱበት፤ ሁልጊዜም እንደተለመደው ታማኝና ፈጣን መረጃዎችን የምናደርስባችሁ፤ ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በፍቅር የምታሳልፉት ይሁንላችሁ!
መልካም አዲስ ዓመት! 🌼🌼

🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼
🍬🎉HAPPY NEW YEAR 🎉🍬
ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ❤️🙏
Seledadotio
Seledadotio
🍬🎉HAPPY NEW YEAR 🎉🍬
ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ❤️🙏
Seledadotio
Seledadotio
Sponsored by
Surafel
1 month ago
ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ዘመን እኛን ይመስላል - አዲስ ዓመት በአዲስ መንፈስ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትናንትን ማደሻ፣ የአዲስ ነገሮች መነሻ ሁሌም ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ከመሆኑም ባሻገር ልዩ የሆኑ ነገሮች ሁሉ የሚጠበቁበት ነው - የዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት
የክረምቱ ወቅት አብቅቶ - መስከረም ሲጠባ፣ አሮጌው ዓመት አልቆ- አዲሱ ዓመት ሲጀምር፣ ምድር በብርሀን ትመላለች፣ በአደይ አበቦች ታጌጣለች፡፡
ሰውም እንደዚሁ የጨለማውን ወቅት ወደ ኋላ ትቶ፣ ዛሬን አቅዶ ነገውን ብሩህ የሚያደርግለትን ተስፋውን አንግቶ ሊራመድ ይነሳል፡፡
ኢትዮጵያ 2018ን በከፍታ አጠናቅቃ ዛሬ 2019 ዓመትን የተሻለ ብሩህ ለማድረግ አልማ ተስፋን ይዛ ወሃ መስከረም ቀን 1 ብላ ጀምራለች፡፡
ነገር ግን እውነተኛ ተስፋ እንዲሁ የሚሳካ ከንቱ ምኞት አይደለም ይልቁን የተገባ ተግባርን የሚፈልግ እንጂ!
አዲስ አመት የሚሰጠን ዕድል እንደ አዲስ መታደስን ፣ ቂምና ቁርሾዎችን በይቅርታ መፍታትን፣ ስብራቶቻችንን መጠገንን ነው፡፡
እንዲሁም ትናንት ዋጋ ካስከፈሉን ስህተቶች የምንማርበትን፣ ነገን ለማሻሻል የምንችልበትን ዕድል ሁሉ ጨምሮ ጨምሮ ይቸረናል፡፡
ታዲያ አዲሱ አመት ባመጣልን ዕድል ነገን አጥርተን ለመኖር ህሊናችንን ዝግጁ ማድረግ ከኛ የሚጠበቅ ሲሆን ሰላምና ደህንነታችንን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት ይፈልጋል፡፡
ሰላም ከሌሎች የሚሰጠን ሳይሆን በእጃችን ላይ ያለ የምንዘራው ዘር ነው፤ እያንዳንዱ ዜጋ በቃልና በተግባር በሚያሳየው የመቻቻል፣ የመከባበርና፣ የይቅር መባባል ተግባር ውስጥ የተሻለ ከዛሬ አልፎ ለነገ የሚተርፍ መልካም ዘርን ይዘራል፡፡
ሰላም፣ የይቅርታና ተስፋ በሚፈጥሩት ውህደት የዜጎች መረጋጋት ይረጋገጣል፤ ይህም በአንድ የጋራ ዓላማ ስር ለመሰለፍ ትልቅ መሰረት ነው፡፡
አዲሱ አመት የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን በጋራ ለመትከልና ለማደግ ሁለተኛ ዕድልን የሚሰጥ በመሆኑ ተስፋችን ፍሬን የሚያፈራው ካለፈው ትምህርት ወስደን ለነገ የሚበጅ የሰላም ዘርን ለመዝራት በሚኖረን ቁርጠኝነት ይሆናል፡፡

"2019 የመከላከያ ሠራዊታችን አቅም ይበልጥ የሚጠናከርበት ዓመት ይሆናል" - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
******************
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ 2018 በርካታ ፈተናዎች የተጋፈጥንበት ዓመት ቢሆንም፣ የመከላከያ ሠራዊቱ የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችንና ዕቅዶችን በተቀናጀ አሠራር በማሳካት የተሰጠውን ኃላፊነት በከፍተኛ ብቃት የተወጣበት ዓመት ነበር ብለዋል።
በተጠናቀቀው ዓመት የሠራዊቱ ዋና ትኩረት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣ ህዝብን መጠበቅና የልማት ጉዞዎችን ከዕንቅፋት መከላከል እንደነበር ጠቁመው፤ በዚህም በተለያዩ አካባቢዎች መረጋጋት በመፍጠር ህዝቡ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ መደረጉን አስረድተዋል።
አክለውም ዘላቂ ሰላም በወታደራዊ አቅም ብቻ የማይረጋገጥ በመሆኑ ህዝቡ ለሰላም የሚያበረክተውን ሚና ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል 2018 ዓ.ም የመከላከያ አቅምን ከዘመኑ ጋር ለማዛመድ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል አሠራር የመሸጋገር፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የመታጠቅ፣ የምድርና የአየር ኃይል አቅምን የማሳደግ እንዲሁም የመከላከያ ኢንዱስትሪን በሀገር ውስጥ ምርቶች የማጠናከር ሰፊ ሥራ የተሠራበት ዓመት መሆኑን ገልፀዋል።
በመጪው 2019 ዓ.ም የመከላከያ ሠራዊቱ ሁለት ዋና ዋና ትኩረቶች ይኖሩታል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የመጀመሪያው የሀገርን ሰላም፣ ደህንነትና ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የሠራዊቱን የማድረግ አቅም፣ የሰው ኃይል፣ የሥልጠና፣ የመሠረተ ልማት እና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ልማት ሥራዎችን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሆነ አስታውቀዋል።
አዲሱ ዓመት የመከላከያ ሠራዊታችን አቅም ይበልጥ የሚጠናከርበትና ዝግጁነቱ የሚያድግበት ዓመት ይሆናል ሲሉም አክለዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ መኮንኖች፣ ወታደሮችና ሲቪል ሠራተኞች መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን ተመኝተው፤ አዲሱ ዘመን ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለህዝባችን ደህንነትና ብልፅግና፣ ለሰራዊታችን የበለጠ አቅም፣ ዝግጁነትና ስኬት የሚያመጣ ዓመት ይሁንልን ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ተወዳጁ እና ዕውቁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለመላው ኢትዮጵያውያን የ2019 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን አስተላልፏል። ድምፃዊው በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው አጭር ነገር ግን ጥልቅ መልእክት፣ መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ዘመን እንዲሆን ተመኝቷል። በተለይም አገሪቱ አሁን ካለችበት ፈታኝ እና አስቸጋሪ ሁኔታ ወጥታ "የኢትዮጵያን ትንሣኤ የምናይበት ብሩህ ዘመን እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ" ሲል ጽፏል። ቴዲ አፍሮ ይህንን የአዲስ ዓመት መልእክቱን ያጠናቀቀው፣ ዘወትር በሚታወቅባቸውና መለያዎቹ በሆኑት "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!" እና "ፍቅር ያሸንፋል!" በሚሉ ቃላት ነው።
የቴዲ አፍሮ የአዲስ ዓመት፣ የበዓላት እና ወቅታዊ መልእክቶች ሁልጊዜም በብዙኃኑ ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቁ እና ትኩረት የሚስቡ ናቸው። በዘንድሮው መልእክቱ ላይ "ኢትዮጵያ ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ ወጥታ" የሚለው አገላለጹ፣ አገሪቱ አሁን ላይ እያለፈችበት ያለውን የጸጥታ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ውጥረት በግልጽ የሚያንጸባርቅ ነው። ቴዲ አፍሮ በሙዚቃዎቹም ሆነ በመልእክቶቹ ዘወትር ለኢትዮጵያ አንድነት፣ አብሮነት እና ለፍቅር የሚቆም አርቲስት እንደመሆኑ መጠን፣ አሁን ላይ ለሕዝቡ እጅግ የሚያስፈልገውን የተስፋ (የትንሣኤ) መልእክት በማስተጋባት አገራዊ ስሜትን አነቃቅቷል።
እውነተኛ የጥበብ ሰው ማለት በክፉም ሆነ በደጉ ጊዜ ከሕዝቡ ስሜት ጋር አብሮ የሚመታ፣ ተስፋ መቁረጥ ሲበዛ የተስፋ ብርሃን የሚያሳይ ነው! ቴዲ አፍሮ ባስተላለፈው መልእክት እንዳስገነዘበው፣ ይህ አዲስ ዓመት የሰላም እና የፍቅር መነሻ እንዲሆን፣ ሁላችንም አገራችንን ከተዘፈቀችበት ፈተና ለማውጣት "ፍቅር ያሸንፋል" በሚለው መርህ ቂም በቀልን ትተን በአንድነት ልንቆም ይገባል! መልካም አዲስ ዓመት!

የበዓሉን ድባብ ሳንለቅ እንዲህ አምሮባቸው የሚታዩትን የሬዲዮ ኦፕሬተር ሰልጣኞች ለትውስታ አጋራናችሁ።
1926 ዓ.ም
አዲስ አበባ
🌼 መልካም አዲስ ዓመት
#ትውስታ #throwbackthursday #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

የቅቤ እቁብ (ዊጂኦ)
ከያሆዴ ድምቀት ጀርባ ያለው ጥበብ
#ethiopia | በወርኃ መስከረም የሀዲያ ምድር በአደይ አበባ ትሸለማለች፤ የክረምቱ ዝናብ ያደፈረሳቸው ምንጮችና ጅረቶች ይጠራሉ። ከከላላሞ ጫፍ እስከ ሾንቆላ ተራራ፣ ከመጨፈራ ዳርቻ እስከ ቦዮ ሐይቅ ወሽመጥ ድረስ ተፈጥሮ ለታላቁ የያሆዴ በዓል ትዘጋጃለች።
ከመስከረም እስከ ህዳር የሀዲያ አውድማዎች በሳቅና በእልልታ ይሞላሉ። የዓመቱ ድካም በደስታ የሚረሳበት፣ የበረከት ወቅት ነው።
ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ድግስና ፈንጠዝያ እንዴት ያለ ኢኮኖሚያዊ ጫና ይከናወናል?
መልሱ “ዊጂኦ” — የቅቤ እቁብ በሚባለው ባህላዊ የቁጠባ ሥርዓት ውስጥ ይገኛል።
የሀዲያ ተወላጅ የሆኑት ወ/ሮ እንዳሻሽ ፀጋዬ ለኢቢሲ ሳይበር እንዳስረዱት፣ የያሆዴ በዓል በአጋጣሚ የሚከወን ድግስ ሳይሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ የቁጠባና የዕቅድ ባህል ውጤት ነው።
የቅቤ እቁብ — ዊጂኦ
የያሆዴ በዓል እንዳበቃ እናቶች ከ4 እስከ 6 ሆነው የቅቤ እቁባቸውን ይጀምራሉ። የሚሰበሰበው ጥሬ ቅቤ በአንዷ እናት ቤት በማሰሮ ውስጥ በጥንቃቄ ይቀመጣል።
ከስድስት ወር በኋላ የበሰለው ቅቤ ይሸጣል፤ በቦታውም አዲስ ቅቤ ይተካል። በዚህ መልኩ የቁጠባው ሰንሰለት ሳይቋረጥ ይቀጥላል።
የእንሰት ቁጠባ — “ሄንቼሳ”
ከቅቤ እቁብ ጎን ለጎን የእንሰት ቁጠባም ይካሄዳል። በደቦ የሚፋቀውና በየጊዜው እየተጨመረ የሚዘጋጀው ቆጮ “ሄንቼሳ” ወይም የዓመት ቆጮ ይባላል።
ነሐሴ ሲገባ እናቶች በዓመቱ ያከማቹትን የቅቤና የቆጮ ድርሻ በፍትሃዊነት ይከፋፈላሉ። መስከረም ሲጠባ ቤታቸው በምግብና በበረከት ሞልቶ እንግዳን ለመቀበል ይዘጋጃሉ።
ዊጂኦ የቁጠባ ሥርዓት ብቻ አይደለም።
ይህ ባህላዊ ሥርዓት የመተማመን፣ የመተሳሰብ፣ የመተጋገዝና አብሮ የመኖር ፍልስፍናን የሚያሳይ የሀዲያ ሕዝብ የኢኮኖሚ ጥበብ ነው።
በዘመናዊ የፋይናንስ ተቋማት በፊት የነበረ ይህ የቁጠባ ባህል፣ በጋራ ጥረት የዓመቱን ድካም ወደ በረከት የመቀየር ጥበብን ያስተምራል።
ዊጂኦ — የገንዘብ ቁጠባ ብቻ ሳይሆን፣ የአንድነት፣ የመከባበርና የአብሮነት መገለጫ!
ከሀዲያ እናቶች ጥበብ እንማር፤ በመተሳሰብና በመተጋገዝ የተሻለ ነገን እንገንባ።
መልካም አዲስ ዓመት!
ናኒ ከሆሳዕና

🌻 አዲሱን ዓመት ማብሰሪያ፣ እንኳን አደረሰን የምንባባልበት:-
📞 የ5 ደቂቃ እና
💬 10 መልዕክቶች በነጻ በስጦታ አበርክተናል!
⏰ ከዛሬ ሌሊት 6:00 ጀምሮ እስከ ነገ ሌሊት 6:00 ሰዓት
🌼 መልካም አዲስ ዓመት!
#ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

የኢትዮጵያውያን ካናዳውያን ቀን በቶሮንቶ በድምቀት ተከበረ
#ethiopia | የኢትዮጵያውያን ካናዳውያን ቀን በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ በመስከረም 5 እና 6 ቀን በድምቀት ተከብሯል።
የዝግጅቱን ድባብ የኢትዮ ፊደል የዩቲዩብ ቻናል በአማርኛ አቀላጥፋ በምትናገር በትውልድ ቻይናዊት በሆነች ታዳጊ አማካኝነት በአዝናኝ ሁኔታ ዘግቧል።
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ የሀገር ናፍቆታቸውን፣ የልጅነት ትውስታቸውን እንዲሁም ለሀገራቸው ያላቸውን መልካም ምኞት ሲገልጹ ውለዋል።
በዝግጅቱ የኢትዮጵያ በዓል ድባብ የተላበሰ ድባብ ተፈጥሯል፤ የባህል ልብስ የለበሱ ታዳሚዎች፣ ቡና የሚያፈሉ እንስቶች፣ የባህላዊ ምግብ ዝግጅትና የሙዚቃ ድግስ ዝግጅቱን አድምቀውታል።
የቶሮንቶ ከንቲባ ኦሊቪያ ቻው መስከረም ወር የኢትዮጵያ የቅርስ ወር መሆኑን በማስታወስ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ካናዳውያን ቡና በጠጡ ቁጥር የቡና መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን ማሰብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
እንዲህ ያሉ ዝግጅቶች የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
ዝግጅቱን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶ እና አካባቢው ነው።
መልካም አዲስ ዓመት!
ሙሉ ቪዲዮውን በኢትዮ ፊደል የዩቲዩብ ቻናል ለመመልከት፦https://youtu.be/JK7T3QeJB...
#ethiopia #canada #toronto #ethiopiannewyear #ethiopianheritage #ethiofidel #ኢትዮጵያ #ካናዳ #ቶሮንቶ #መልካምአዲስአመት

🏆 አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
የአዲስ ዓመትን የተሳትፎ ውድድር በመሳተፍ ምላሽ ካገኙ ውስጥ ለ300 ዕድለኞች 10 ጊ.ባ ወርኃዊ የኢንተርኔት ጥቅል ሽልማት እናበረክታለን!
አሸናፊዎች በ24 ሰዓት ውስጥ የስልክ ቁጥር ባሸነፋችሁበት ገጽ በውስጥ መልዕክት ይላኩልን።
አብራችሁን ስለነበራችሁ እናመሰግናለን!
🌼 መልካም አዲስ ዓመት!
የአሸናፊዎች ዝርዝር: https://t.me/telebirr/8478
#ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
የአዲስ ዓመትን የተሳትፎ ውድድር በመሳተፍ ምላሽ ካገኙ ውስጥ ለ300 ዕድለኞች 10 ጊ.ባ ወርኃዊ የኢንተርኔት ጥቅል ሽልማት እናበረክታለን!
አሸናፊዎች በ24 ሰዓት ውስጥ የስልክ ቁጥር ባሸነፋችሁበት ገጽ በውስጥ መልዕክት ይላኩልን።
አብራችሁን ስለነበራችሁ እናመሰግናለን!
🌼 መልካም አዲስ ዓመት!
የአሸናፊዎች ዝርዝር: https://t.me/telebirr/8478
#ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
1 month ago
በፋንታ መኪና እየተሸለሙ በነፃ ይጓዙ! የት እንምጣ?
🎉 አዲስ አበባ በአዲስ ዓመት ከፋንታ ጋር እየደመቀች ነው! 🎉
ተወዳጁ ፋንታ እንደተለመደው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በጳጉሜ ወር በሙሉ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚገኙ ተሳፋሪዎች የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል!
በጉዞው ወቅት ምን ይጠብቅዎታል?
🚌 ነፃ ጉዞ: ከፒያሳ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ፣ መርካቶ፣ ኮዬ፣ አያት፣ ሱሉልታ፣ ጣፎ፣ ጀሞ፣ ቃሊቲ እና ወደ ሌሎችም አካባቢዎች የሚደረጉ ጉዞዎች ሙሉ በሙሉ ነፃ ናቸው!
🐔 የበዓል ሽልማቶች: በአውቶቡስ ውስጥ በሚደረጉ አዝናኝ ጨዋታዎች ለሚሳተፉ መንገደኞች ዶሮዎች፣ እንቁላሎች እና ሌሎች የበዓል ስጦታዎች ይበረከታሉ።
🎭 መዝናኛ: ከታዋቂ ቲክቶከሮች እና ኮሜዲያኖች ጋር በሚደረጉ ጨዋታዎች፣ ጥያቄዎች እና ቀልዶች ከመነሻ እስከ መድረሻዎ ፈገግታ እንደበራ ይጓዛሉ።
👇 ፋንታ አሁንም “የት እንምጣ?” እያለዎት ነው!
የፋንታ አውቶቡስ ወደ እርስዎ ሰፈር እንዲመጣ ይፈልጋሉ? ያሉበትን አካባቢ አሁኑኑ ኮመንት ላይ ጻፉልን፤ እኛ ወደ እርስዎ እንመጣለን!
መልካም አዲስ ዓመት! ከፋንታ ጋር በነፃ ይጓዙ፣ ይጫወቱ፣ ይሸለሙ!
#fantaethiopia #addisababa #fantafreetransportaddis #enkutatash2019 #fantabusactivation #ethiopiannewyear #fantagiveaway

አዲስ አበባ በአዲስ ዓመት ከፋንታ ጋር እየደመቀች ነው!
ተወዳጁ ፋንታ እንደተለመደዉ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ጳጉሜ ወር በሙሉ በመዲናችን አዲስ አበባን ለማህበረሰባችን በነፃ ትራንስፖርት በመስጠት ላይ ይገኛል!
በዚህ ልዩ የበዓል ጉዞ በአውቶቢስ ውስጥ የተለያዩ የበዓል ሽልማቶችን እየሸለመ፣ በተለያዩ አዝናኝ ጨዋታዎች፣ ተሳፋሪዎች እያዝናና ከመነሻ እስከ መድረሻችሁ ጥርሳችሁን ሳትከድኑ እያደረሳችሁ ይገኛል። የትናችሁ ፒያሳ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ፣ መርካቶ፣ ኮዬ፣ አያት፣ ሱሉልታ፣ ጣፎ፣ ጀሞ፣ ቃሊቲ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚደረገው ጉዞ ሙሉ በሙሉ ነፃ ከመሆኑም በላይ፣ በጨዋታዎቹ ለሚሳተፉ መንገደኞች ዶሮዎች፣ እንቁላል እና ሌሎችንም የበዓል ስጦታነት እያበረከተ ይገኛል።
በአውቶቡሱ ውስጥ ከታዋቂ ቲክቶከሮችና ኮሜዲያኖች ጋር በሚደረጉ ጨዋታዎችና ጥያቄዎች ጉዞዎን ያደምቁ! ፋንታ አሁንም “የት እንምጣ?” እያለዎት ነው፣ አውቶቡሱ ወደ ሰፈራችሁ እንዲመጣ የምትፈልጉበትን አካባቢ ኮመንት ላይ ጻፉልን፤ ያላችሁበት እንመጣለን።

አዲስ ዓመት፣ አዲስ ስኬት!
ሕይወትዎን፣ ቢዝነስዎን እና የገንዘብ አያያዝዎን መቀየር ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ «ሕይወትና ስኬት» የተሰኘውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።
በዚህ ቻናል፦
አስደማሚና አነቃቂ የስኬት ታሪኮች
የዓለማችን ታላላቅ ሥራ ፈጣሪዎች የሕይወት ጎዳና
ቢዝነስና ገንዘብን ማስተዳደሪያ ጠቃሚ ሃሳቦች እና መረጃዎች ይቀርባሉ።
እውቀትን ከጥልቅ ግንዛቤ ጋር በማቀናጀት ሕይወትዎን ለማሻሻል አሁኑኑ የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 ቻናሉን ለመቀላቀል እዚህ ይጫኑ; Hiwotenasiket

Comments