Logo
AHADU RADIO FM 94.3
2 hours ago
ካፒታል ሆቴል እና ሆሴ ሪል እስቴት ለሜቄዶንያ ከ4 ሚሊዮን ብር  በላይ ድጋፍ አደረጉ

መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) መስከረም 29 "የካፒታል ሆቴል ቀን" ተብሎ መሰየሙን የሜቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር ገልጿል።
 
ካፒታል ሆቴል ከሆሴ ሪል እስቴት ጋር በመተባበር ለማህበሩ በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት በአጠቃላይ የ4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የሜቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር አስታውቋል።
​
የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ አ/ቶ ተስፉ ፍፅም እንደገለጹት፤ ሆቴሉ በጥሬ ገንዘብ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲሁም በዓይነት 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።

በተጨማሪም ሆሴ ሪል እስቴት የ2 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል ።

​ከዚህ በተጨማሪም ከ350 በላይ የሚሆኑ የካፒታል ሆቴል ሰራተኞች እና አስተዳደር አባላት ከደመወዛቸው በመለገስ ማህበሩን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል ።
​
የሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች ቢንያም በለጠ በበኩላቸው፣ ተቋማቱ እና ሰራተኞቻቸው ላደረጉት ቀጣይነት ያለው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ማህበሩ ቋሚ የውጭ ፈንድ ወይም ገቢ የለውም ያሉት መስራቹ ከ9 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመመገብና ለመንከባከብ የሁሉም አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

በደረጄ መንግስቱ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
AHADU RADIO FM 94.3
6 hours ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ወደ ታሪካዊ ስፍራው ተመልሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የተቋሙ መነሻ እና ታሪካዊ ስፍራ የሆነው ብሔራዊ ፓስታ ሙዚየም ወደ ቀድሞው እና ታሪካዊ ቦታው ተመልሶ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን መደረጉን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም " አንድ የፖስታ አውታረ መረብ ገደብ የለሽ ዕድሎች " በሚል መሪ ቃል የዓለም የፖስታ ቀንን ባከበረበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስት ሙዚየም በዋናው የፖስታ አገልግሎት ተቋም ውስጥ ከ50 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥና ታሪካዊ ነገሮችን ለጎብኚዎች ሲያስተዋውቅ እንደነበር የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦትና አስተዳደር ሃላፊ አ/ቶ ጋሻው መርሻ ተናግረዋል።

በተለይም ከዛሬ ጀምሮ ክፍት የተደረገው ይህ የብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ለተማሪዎች ፣ ለተመራማሪዎች እንዲሁም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ አገር ጎብኝዎች ምቹ በሆነ ሁኔታ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አብራርተዋል።

የማሻሻያ ስራው የታሪክ ቁሳቁሶችን እና የቴምብር ስብስቦችን ለጎብኚዎች በጥራት ለማቅረብ እንዲሁም የዲጂታል እና የተቋሙ ሀብቶችን በጥቅም ላይ በማዋል ዘመናዊ እና ምቹ አከባቢን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።

ታሪክን ጠብቆ ማቆየትና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የተቋሙ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የተደረገው በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት እምብርት እና የሀገሪቱ የመገናኛ ታሪክ የጀመረበት ትልቅ ታሪካዊ ቦታ ላይ ነው ብለዋል።

በተመስገን ተጋፋው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ