Logo
Getu Temesgen
ታላቅ ውጤት በሰርከስ ጥበብ ከአገረ ሩሲያ 🇷🇺
#ethiopia | የብላክ ላየን ሰርከስ ቡድን የሆነው ትሩፕ አዲስ አበባ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ በተካሄደው የሰርከስ ኒውክሊን /Nikulin Circus Moscow/ እጅግ ድንቅ በሆነ አቀራረብና ፉክክር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ይህ ቡድን በባለፈው አመት በፈረንሳይ በተካሄዱት የዓለማችንን አንጋፋው ሰርከስ ፌስቲቫል ሰርከስ ሞንቴካርሎ/Cirque Monte Carlo/ ላይ የነሃስ አንዲሁም በቦርዴክ አለም አቀፍ ፌስቲቫል/11th Cirque de Bayeux,France/ ላይ የወርቅ ዋንጫ አሸናፊ መሆን የቻለ ድንቅ የሰርከስ ቡድን መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቡድኑ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ፕሬዚዳንት አርቲስት ተክሉ አሻግሬና በአዲስ አበባ ሰርከስ ማህበር ም/ፕሬዚዳንት አርቲስት ቢኒያም እንዳለ አቀባበል ተደርጎለታል።

እንኳን ደስ ያላቹ ! እንኳን ደስ ያለን! 🇪🇹 🇷🇺

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.