Logo
Getu Temesgen
አሜሪካና ቻይና በቲክ ቶክ ላይ ስምምነት ደረሱ !!
#ethiopia | ዋሽንግተንና ቻይና በቲክ ቶክ ባለቤትነት ማዕቀፍ ላይ ስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል ።

በድርድሩ የተሳተፉት የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት እንዳስታወቁት ቲክቶክ በአሜሪካ ያለውን የባለቤትነት ድርሻ በተመለከተ በማድሪድ የተደረገው ወይይት አመርቂ ውጤት አስገኝቷል።

በማድሪድ የተደረገው የንግድ ንግግር በቲክ ቶክ ላይ ለአሜሪካ ባለቤትነት መንገድ ለመክፈት ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የፊታችን አርብ ስምምነቱን ያጸናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቻይና በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ከመስጠት መቆጠቧን ድርድሩን ተከትሎ የወጣው መረጃ ያሳያልል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
#kgethiopia

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.