ኳታር እና አሜሪካ ስለእስራኤል ጥቃት
#ethiopia | የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት እስራኤል በዶሃ ያደረሰችውን ጥቃት በተመለከተ ለመምከር ተገናኙ።
የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱራህማን ቢን ጃሲም አልታኒ በዚህ ሳምንት እስራኤል በዶሃ ላይ በፈጸመችው ከባድ ጥቃት ዙርያ ለመምከር በኒውዮርክ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተዋል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ባሳለፍነው ማክሰኞ እስራኤል በዶሃ የጋዛ ጦርነትን ለማስቆም በትራምፕ በቀረበው አዲስ ስምምነት ላይ ሲወያዩ የነበሩ አምስት የሃማስ አባላትን እና የኳታር የደህንነት ባለስልጣን ጥቃት ሰንዝራ መግደሏን ተከትሎ ነው ከትራምፕ ጋር ለመመካከር የተገናኙት ብለዋል።
ከትራምፕ ጋር ከሚደረገው የእራት ስብሰባ በፊት ሼክ መሀመድ፥ ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በዋይት ሀውስ ተገናኝተው በእስራኤል ጥቃት እና በአሜሪካ እና በኳታር የፀጥታ ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
ዋሽንግተን ኳታርን እንደ ጠንካራ የባህረ ሰላጤ አጋር ትቆጥራታለች።
እስራኤል በኳታር ላይ እያነጣጠረች ያለው ጥቃት የእስራኤል-ሃማስ የተኩስ አቁም ንግግር ለማደናቀፍ የተነደፈ ነው ሲሉ ትራምፕ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ
ዶሃ በሰሜናዊ ኳታራ የተፈፀመውን የማክሰኞው ጥቃት፥ ህገ- ወጥ የወንጀለኞች ድርጊት እና ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ቴል አቪቭን ወንጅላለች ፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ጥቃቱን የኳታርን ሉዓላዊነት የጣሰ ነው ሲሉ አውግዘዋል ፡፡ይሁንና የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ቢሮ የሃማስን መሪ ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው በሚል አስተባብሎ እንደነበር ይታወሳል።#nbc

9 months ago