Logo
FastMereja
እናት ባንክ ለፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ስጦታ አበረከተ
#fastmereja I አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ እናት ባንክ ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም ለፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

እንቁጣጣሽን ከፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ያከበሩት እናት ባንክ ከህብረተሰቡ ጋር አብሮ በዓልን በማሳለፍ የመረዳዳትና እሴትን ማጎልበት ዓላማ እንዳደረገ ተገልጿል።

እናት ባንክ ከባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ባንኩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም ለአዲስ አመት በዓል መዋያ ለእናቶች የገንዘብ ስጦታ ተደርጓል።
#ማህበራዊ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.