Logo
YenetaTube
ለታላቁ ስብሰባ ወደ አህጉረ አፍሪካ ድርሽ አልልም !/ዶናልድ ትራምፕ/

‎የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳር ወር በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ በተያዘው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ እና በምትኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እንደሚልኩ ተናገሩ ።

‎የቡድኑን ተለዋጭ የፕሬዚዳንትነት ቦታ በመያዝ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን የቡድን 20 ጉባኤ ለመዝለል ለምን እንደወሰኑ የገለፁት ትራምፕ ሀገሪቱ ለአሜሪ ፖሊሲዎች
‎ከፍተኛ ንቀት እንዳላትና ይልቁንስ ከሩሲያና ቻይና ጋር እያሴረች ትገኛለች እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ አናሳ ነጭ ገበሬዎች ላይ “ዘር ማጥፋት” እየተካሄደ ነው በማለት በደቡብ አፍሪካ መንግስት ላይ ተከታታይ ውንጀላዎችን አቅርበዋል።

‎በተጨማሪም ትራምፕ በፍሎሪዳ በሚገኘው ማር-አ-ላጎ እስቴት አቅራቢያ በሚገኘው የጎልፍ ሪዞርታቸው ከደብቡ አፍሪካ ቀጥሎ የሚቀጥለውን ዓመት G20 የመሪዎች ጉባኤ አሜሪካ በመሆኗ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

‎ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በሚቀጥለው አመት በፍሎሪዳ በሚካሄደው የ G20 የአለም መሪዎች ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ያላቸውን ጉጉት ገልፀዋል ።

‎ምንም እንኳን ሁለቱም የሚመሩት ሀገራት የቡድኑ ሙሉ አባላት ቢሆኑም ትራምፕ ግን ፑቲን እና ዢ ሊገኙ ይችሉ እንደሆነ ሲጠየቁ "እወዳቸዋለሁ" እና እንደ "ታዛቢዎች" መሳተፍ እንደሚችሉ ተናግረዋል ።

‎አክለዉም ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጃፓን እና ሩሲያን ጨምሮ ከታላላቅ ኢኮኖሚ ቡድን የተውጣጡ መሪዎችን ሲያስተናግድ "የእኛን አስደናቂ ስኬት ለአለም ለማሳየት እጓጓለሁ።" ብለዋል ።

‎G20 ሩሲያ እና ቻይና እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት (አህ) እና የአፍሪካ ህብረትን ያካትታል ነገር ግን በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የተሰጠ የጦር ወንጀል የእስር ማዘዣ ፑቲን ባለፈው አመት በብራዚል በተካሄደው ዝግጅት ላይ አልተገኙም ሲል ያስነበበዉ CBC የዜና ወኪል ነዉ።


‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ




10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.