" የመንግስት በጀት በጥቂት ግብር ከፋዮች ጫንቃ ላይ ወድቋል " - ቴዎድሮስ መኮነን (ዶ/ር)
#ethiopia | የግሉ ዘርፍ በተጣበበ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ 90 በመቶ ዓመታዊ የመንግስት በጀት የሚደገፈው ከጠቅላላ ግብር ከፋዮች ውስጥ 10 በመቶ በታች በሆኑ ጥቂት ግብር ከፋዮች መሆኑን ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ምርምር ያደረጉት የኢኮኖሚ ባለሙያው ቴዎድሮስ መኮንን (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ይህን የገለጹት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ " ሚድሮክ ለሃገር ! " በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ ከቀናት በፊት ባዘጋጀው አውደርዕይ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ጎን ለጎን በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ነው።
የኢኮኖሚ ባለሙያው የግሉ ዘርፍ በአንዳንድ ማህበረሰቦች ዘንድ " አጭበርባሪ " ተብሎ ስለሚታሰብ የሀገራችንን እድገት በከፍተኛ ሁኔታ እንደጎዳው እና እየጎዳው መሆኑን ተናግረዋል።
ቴዎድሮስ መኮነን (ዶ/ር) በዝርዝር ምን አሉ?
" እ.ኤ.አ በ2017 በሀገር አቀፍ ደረጃ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ (business registration) ወደ 50ሺህ ገደማ ነበር። በ2023 ደግሞ ከ 200ሺህ በላይ ነው፣ አሁን ላይ ያለው ትክክለኛ ቁጥራዊ መረጃ ባይኖርም በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር እንደሚችል ማወቅ ይቻላል።
ከዚህ ውስጥ 78 በመቶ license የወጣው በሁለት ሴክተሮች ብቻ ነው፣ እነዚህም ንግድ እና ትራንስፖርት ናቸው። ይህ የሚያሳየው የግሉ ዘርፍ ያጋደለበትን የስራ ዘርፍ ነው። የሀገራችንን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይመራል ተብሎ የሚታሰበው የግሉ ዘርፍ ነው። ነገር ግን የግሉ ዘርፍ አጭበርባሪ ነው ተብሎ ይታሰባል። ይህ የተሳሳተ ሃሳብ የሀገራችንን እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል።
የሀገራችንን ኢኮኖሚ የተሸከሙት ጥቂት ድርጅቶች ናቸው፣ 90 በመቶ ታክስ የሚከፍሉት 10% በታች የሆኑ ታክስ ከፋዮች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አንዱ ነው። የሀገሪቱን የመንግስት በጀት የመደገፍ ጫና በጥቂት ድርጅቶች ጨንቃ ላይ ወድቋል።
ይህ የሚያሳየን የግሉ ዘርፍ በምን ያህል በተጣበበ ሁኔታ ውስጥ እንዳለና ገና ብዙ ማደግ እንዳለበት ነው። በጥቂት ግብር ከፋዮች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ከተፈለገ የታክስ ቤዙ (tax base ) መስፋት አለበት። " ብለዋል።
ሌለኛው የፓናል ውይይቱ ተናጋሪ የኢኮኖሚ ባለሙያና የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) " የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስትራክቸራል ትራንስፎርሜሽን ማሳየት አለበት ከተባለ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪው፣ ከኢንፎርመል ወደ ፎርማል መምጣት ያስፈልጋል " ብለዋል።
አክለው " አሁን ባለንበት ሁኔታ ግብርና እየቀነሰ መጥቶ መደበኛ ያልሆነውን ጨምሮ ወደ 62.4 በመቶ employment ይዟል። ኢንዱስትሪውን ስንመለከት ደግሞ 6.5 በመቶ ብቻ ነው። ስለዚህ ሰርቪሱ 31.2 በመቶ የያዘበት ሁኔታ ነው ያለው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ወደ ሚድሮክ ስንመጣ ከ 79ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞችን በቋሚነት ቀጥሯል። ይህ የሚያሳየው ፎርማል የሆነውን ዘርፍ በማሳደግ በኩል ሚድሮክ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሸሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀገራችን በግሉ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ክፍተቶች መኖራቸውን እና የገበያ እይታ የተዛነፈ መሆኑን ገልፀዋል።
" የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ የመሪነት ድርሻ ያልተጫወተበት ሀገር ኢኮኖሚው ከእጅ ወደ አፍ የዘለለ ወይም ኋላ ከመቅረት ያለፈ አይሆንም " ብለዋል።
" ሀገራችን ያለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እና ዳጎስ ያለ ድርሻ ያላቸው ኢንቨስተሮችን ያላሳተፍን እንደሆነ የምንፈልገው እድገት በፍጥነት ማረጋገጥ ስለማንችል እይታችን ሀገር በቀል እና የውጭ ባለሃብቶች ላይ መሆን አለነት ፤ ሊደገፉም ይገባል " ሲሉ ጠቁመዋል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

9 months ago