Logo
Getu Temesgen
አቅመ ደካሞችን መደገፍ የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው - አቶ ኦርዲን በድሪ
#ethiopia | አቅመ ደካማ ዜጎችን መደገፍ የወንድማማችነት እና እህትማማችነት ስሜትን የሚያዳብር የሰው ተኮር እሳቤያችን ማሳያ ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የመውሊድና የዘመን መለወጫ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ከ1 ሺ በላይ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች ማህበራዊ ትስስርን የሚያጎለብቱና የአብሮነት እሴቶች እንዲዳብሩ የሚያስችሉ በመሆናቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የምንታወቅበትን የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ባህል ይበልጥ በማጎልበት ከአቅመ ደካማ ዜጎች ጎን ልንቆም ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቴዎድሮስ ታደሰ
#etv #harari #ማዕድማጋራት

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.