ሃገር በቀል የሆነው የኢኮሜርስ ፕላትፎርም ቲና ማርት አንጋፋ ከሆነው ኢትዮ ፖስት ጋር ሃገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ኦፕሬሽን ማከናወን የሚያስችል ስምምነት ተደረገ።
#ethiopia | ዛሬ በዴ-ሊኦፖል ሆቴል የተካሄደው ይህ የስራ ውል ስምምነት የቲና ማርትን ሃገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ኦርደሮች በኢትዮ ፖስት በኩል ማድረስ የሚያስችል የሎጀስቲክስ (ዴሊቨሪ) ስምምነት ሲሆን፡ ስምምነቱ የኢትዮ ፖስት ዋና የንግድ ሥራ ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በቀለ እና የቲና ማርት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆነው ኢዘዲን ካሚል ፈርመውታል።
በዚህ ታሪካዊ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ ከሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የስራ ባለ ድርሻ አካላቶች የተገኙ ሲሆን፡ ኢትዮ ፖስት ለሃገር አቀፍ የኢኮመርስ እድገት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው እና ተቋሙ ሊመሰገን እንደሚገባ የቲና ማርት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢዘዲን ካሚል ገልጿል። ወ/ሮ ትግስት አክለውም ተቋማቸው ለሃገር በቀል ኢኮሜርስ እድገት እና ዲጂታላይዜሽን ዳጋፍ እንደሚሰጡ እና ከቲና ማርት ጋር የተደረገው ይህ ውል ምሳሌ እንደሆነ አውስተዋል።
ቲና ማርት
ትንሽ ክፍያ፣ ብዙ ሸመታ!

9 months ago