Logo
FIDEL POST NEWS
በቤጂንግ በተካሄደ ሰልፍ ላይ ፑቲን እና ሺ ከ150 ዓመት በላይ ስለመኖር ተነጋገሩ

በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተካሄደ ወታደራዊ ሰልፍ ላይ የዓለም መሪዎች ያደረጉት ልዩ ውይይት 'በሆት ማይክ' ተይዟል።

በዚህ ውይይት ወቅት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የሰውን ልጅ እድሜ እስከ 150 ዓመት ስለማራዘም እና የአካል ክፍል ንቅለ ተከላ ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን አመለካከት ገልጸዋል።

እኚህ ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና ከተለያዩ ሀገራት ልዑካን ጋር በመሆን ወደ ቲያናንመን አደባባይ ሲጓዙ የነበረ ሲሆን፣ ክስተቱ የተፈፀመው ረቡዕ ነው።

የቻይናው የመንግስት ቴሌቪዥን ሲሲቲቪ ዝግጅቱን በቀጥታ ሲያስተላልፍ፣ ከ1.9 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ የኦንላየን ተመልካቾች እና ከ400 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የቴሌቪዥን ተመልካቾች እንደተመለከቱት ተገልጿል።

በዚህ ጊዜ የፑቲን አስተርጓሚ በቻይንኛ ቋንቋ "የባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለማቋረጥ እየተሻሻለ ነው" ሲል ይሰማል።

ሆኖም የሺ ንግግር በሚደረግበት ወቅት ካሜራው ወደ አደባባዩ በስፋት አጉልቶ በማሳየቱ ድምፁ በራስ-ሰር ጸጥ ብሏል። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሶስቱ መሪዎች ወደ ካሜራው ተመልሰው ወደ ሰልፉ መድረክ ደረጃዎች ሲወጡ ታይተዋል።

በኋላም ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ የውይይቱ ትክክለኛነት አረጋግጠዋል። "ወደ ሰልፉ ስንሄድ ሺ ጂንፒንግ ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሩ አስታውሳለሁ" ብለዋል። "ዘመናዊ ሕክምና፣ የቀዶ ሕክምና ሂደቶች እና የአካል ክፍሎች ንቅለ ተከላ የሰዎችን ንቁ ህይወት ለማራዘም አዲስ ተስፋ እየፈጠሩ ነው" ሲሉም አክለዋል።
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.