የምዕራባውያን እኛ ብቻ አካሄድ እናወግዛለን ! /ቻይናና ሩሲያ /
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት የሆኑት ቻይና እና ሩሲያ ከአስር አመታት በፊት በኒውክሌር ስምምነት መሰረት የተፈታውንና ለተወሰኑ ጊዜ ተነስቶ የነበረዉን በቴህራን ላይ የተወሰደ የ ማዕቀብ እርምጃ የአውሮፓ ሀገራት እንደገና ለመጣል የወሰዱትን እርምጃ ውድቅ ማድረጓን እንደሚደግፉና ከኢራን ጎን እንደሚቆሙ መናገራቸው ተሰማ ።
በብሪታንያ ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ማዕቀቡን ወዲያውኑ ለማደስ የወሰዱት እርምጃ “የማቅለሽለሽ ጨቋኝ ዘዴ” ተብሎ በሚጠራው “በሕጋዊ እና በሥርዓት ጉድለት” ነው ሲሉ የቻይና፣ ሩሲያ እና ኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተፈረመ ደብዳቤ ላይ ገልፀዉታል ።
የነገሩ ጅማሮ እንዲህ ነበር እ.ኤ.አ. በ2015 ከዓለም ኃያላን ሀገራት የኒኩሊየር ጉዳይ ስምምነት ነበራቸው በስምምነቱም ቻይና ፣ ሩሲያና ኢራን ከሦስቱ የአውሮፓ ሀገራት ጋር ፈራሚዎች ይገኙበት የነበረ ነገር ግን የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸዉ እ.ኤ.አ. በ2018 አሜሪካን ከስምምነቱ በማስወጣት አውሮፓውያን የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በመገደብ ኢራንን በመወንጀል የማዕቀብ መአት አወረዱባት ኢኮኖሚዋን ያሽመደምዱት ገቡ ቴህራን ግን ጫናዉን በመቋቋም መርሀ ግብሯን ቀጥላ ዛሬ ላይ ደረሰች ይህም ያሳሰባቸው ሀገራት
ከአለም አቀፍ የገንዘብ ማዕቀብ እፎይታ ያስገኘላትን ስምምነቱን በመጣስ ኢራንን በመወንጀል "የመመለስ ዘዴ" ባለፈው ሳምንት ጀምረዋል ።
በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ እስራኤል እና ዩኤስ የኢራን የኒውክሌር ግንባታዎችን ቦምብ ካደረሱ በኋላ ኢራን እና ኢ3 አዲስ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ያነጣጠረ ውይይት አድርገዋል ይህን ተከትሎ ባወጡት መግለጫ ዳግም በኢራን ላይ መአቀብ ለመጣል መታሰቡ በጭራሽ እንደማይቀበሉት ገልፀዋል ።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ ሰኞ ዕለት በኤክስ ላይ በለጠፉት ደብዳቤ ላይ በብሪታንያ ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን የወሰዱት እርምጃ "የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ስልጣንን እና ተግባራትን አላግባብ ይጠቀማል" ብለዋል ።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤክስ ላይ በሰጡት መግለጫ “ከባልደረቦቼ፣ ከቻይና እና ሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በቲያንጂን የተፈራረሙት የጋራ ደብዳቤ፣ አውሮፓውያን ድንገተኛ ጥቃት ለመሰንዘር የሚደረገው ሙከራ በህጋዊ መልኩ መሠረተ ቢስ እና ፖለቲካዊ አጥፊ ነው የሚለውን ጽኑ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው” ብለዋል ሲል የዘገበው ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago