Logo
Getu Temesgen
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይያዙ
#ethiopia | የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲሄዱ ገቢዎች ሚኒስቴር አሳሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ የወጪ መጋራት ተጠቃሚ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት እንዳለበት አስታውሷል።

ሚኒስቴሩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ በአካባቢያቸው በሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት (ገቢዎች) ወይም ቢሮ በመቅረብ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እንዲያወጡ ሚኔስቴሩ አሳስቧል።

ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚገቡበት ወቅት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲቀርቡ አስገንዝቧል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.