የኢኳቶሪያል ጊኒ የቀድሞ ባለስልጣን ባልታሳር ኤንጎንጋ በወሲብ ፊልም ቅሌትና በገንዘብ ምዝበራ የ8 ዓመት እስር ተፈረደባቸው
የኢኳቶሪያል ጊኒ ፍርድ ቤት ረቡዕ ባልታሳር ኤባንግ ኤንጎንጋ የተባሉ ከፍተኛ ባለሥልጣንን በገንዘብ ምዝበራ ወንጀል የስምንት ዓመት እስራት የፈረደ ሲሆን፣ እኚሁ ባለስልጣን ደግሞ ከሌሎች ባለስልጣናት ሚስቶች ጋር በተቀረጹ የወሲብ ፊልሞች ብዙዎችን ቅር አሰኝተው ነበር።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬስ ዳይሬክተር ሂላሪዮ ሚቶጎ በዋትስአፕ መልእክት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ የባዮኮ ግዛት ፍርድ ቤት ባልታሳር ኤባንግ ኤንጎንጋ ለግል ጥቅም ሲሉ የሙያ ጉዞ ወጪ ተብሎ በጠየቁት ገንዘብን ወንጀለኛ መሆኑናቸውን አረጋግጧል።
ባለትዳርና የቀድሞ የብሔራዊ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ኃላፊ የነበሩት ኤንጎንጋ ከአምስት ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን በነዳጅ በበለጸገችው መካከለኛው አፍሪካዊት ሀገር በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር አባክነዋል ተብለው ተከሰው ነበር።
“ቤሎ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ኤንጎንጋ የገንዘብ ምዝበራ ወንጀልን ተከትሎ በእስር ላይ እንዳሉ፣ አንዳንዶቹ በፋይናንስ ሚኒስቴር ቢሮው ውስጥ የተቀረጹ የግብረ ስጋ ግንኙነት ቪዲዮዎቻቸው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ባለፈው ህዳር ወር በአለም አቀፍ ደረጃ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር።
ቪዲዮዎቹ “ባልታዛሪየም” የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን አስቂኝ ዘፈኖችንና ዳንሶችን ጨምሮ በርካታ የኦንላየን ላይ ገለጻዎችን ቀስቅሰዋል።
ሚቶጎ እንደተናገሩት የክልሉ ፍርድ ቤት በኤንጎንጋ ላይ የ8 ዓመት እስራት እና የ220,000 ዶላር ቅጣት ጥሏል።

9 months ago