Logo
Getu Temesgen
መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን 35 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዕቅዱ አጠፈ
#ethiopia | መንግሥት በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ መሠረት የኢትዮ ቴሌኮምን 35 በመቶ ድርሻ ለውጭ ኩባንያዎች ለመሸጥ ማቀዱ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ግን ዕቅዱን ማጠፉ ታወቀ፡፡

ሪፖርተር ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንዳስነበበው መንግሥት ለውጭ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያሰበው ዕቅድ በቅርብ ዓመታት ተግባራዊ አይደረግም ፡፡

በቀጣይ የኩባንያውን ተጨማሪ ድርሻ ለመሸጥ ‹‹በመጀመሪያ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተሸጠው ድርሻ ምን ያህል ያዋጣል?›› የሚለው መታየት እንደሚኖርበት፣ በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ድርሻ ለውጭም ሆነ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የመሸጥ ዕቅድ እንደሌለና በቅርብ ጊዜ ውስጥም እንደማይኖር አስታውቀዋል፡፡
#kgethiopia

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.