Logo
FIDEL POST NEWS
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ2026 የዓለም ዋንጫ ዕጣ ድልድል በፈረንጆቹ ታህሳስ 5 ቀን 2025 በዋሽንግተን ዲሲ ይከናወናል አሉ

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ሲያስታውቁ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋቲኖ እና የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ተገኝተዋል።

የዕጣ ድልድሉ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኬኔዲ ማዕከል እንደሚደረግ ማስታወቃቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ጣምራ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን የ48 ሀገራት የእግርኳስ ብሔራዊ ቡድኖች በመድረኩ ይሳተፋሉ፡፡
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.