' እኔ ቀይሬያለሁ : አንተ ግን ያንኑ ነው የለበስኸው '
#ethiopia | ብሪያን ግሌን እድሜው በሃምሳዎቹ አጋማሽ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው። የዋይት ሃውስ ቋሚ ዘጋቢ ሆኖ እየሰራ ነው ። የሚሰራበት የቴሌቪዥን ጣቢያ RAV( Real America's Voice )ቀኝ ዘመም ወግአጥባቂ ሚዲያ ነው። ጋዜጠኛ ብሪያንም ሚዲያውም ቀንደኛ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ደጋፊ ናቸው።
.
ከአምስት ወራት በፊት የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ በነጩ ቤተመንግሥት ከትራምፕ ጋር በቀጥታ ስርጭት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ደስ የማይል ጊዜ አሳልፈዋል።
በጊዜው ዘሌንሲኪ የማንኛውም አገር መሪ ላይ ሊደረግ በማይገባ ሁኔታ ያስተናገዷቸው ፕሬዚዳንት ትራምፕና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ብቻ አልነበሩም። የእነርሱ ደጋፊ ጋዜጠኞችም ጭምር ነበሩ።
.
አንዱ ብሪያን ግሌን ነበር ። በወቅቱ እንዲህ ብሎ ጠይቋቸው ነበር ...."እንዴት ሙሉ ልብስ አይለብሱም ?! በዚህ አገር በትልቁ ቢሮ ውስጥ ነው የሚገኙት ነገር ግን ሙሉ ልብስ ለመልበስ አሻፈረኝ ብለዋል ...ለመሆኑ ሙሉ ልብስ አሎት ?! "
.
ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ 'ጦርነት ላይ ያለሁ መሪ ነኝ ..ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ሙሉ ልብስ እለብሳለሁ ' ብለው መለሱለት።
..
ከአምስት ወር በኋላ ዛሬ ምሽት ዘሌንስኪ በድጋሚ ነጩ ቤተመንግሥት ተገኝተው ነበር ። ከባለፈው ትምህርት የወሰዱ ይመስላል። ሁሉ ቦታ ወታደራዊ ቲሸርት የሚለብሱት ፕሬዝደንት ሸሚዝ ለብሰዋል ። ጃኬት ደረብ አድርገዋል።
.
ጋዜጠኛ ግሌን የጥያቄ እድል ሲሰጠው በድጋሚ አለባበሳቸውን አነሳ ።
' ዛሬ በዚህ ልብስ በጣም አምሮብዎታል ' አላቸው ። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ' እኔም ተመሳሳይ ነገር ብዬዋለሁ ' ካሉ በኋላ ይህ እኮ ነው ባለፈው የተናገረህ ጋዜጠኛ ብለው አስታወሷቸው ።
ግሌን ' ይቅርታ እጠይቃለሁ : ግሩም ሆነዋል ' አለ ...
.
ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ አቋርጠውት ' እኔ ቀይሬያለሁ : አንተ ግን ያንኑ ነው የለበስኸው አልቀየርህም ' ብለው ቀለዱ።
.
በወቅቱ ቢቢሲ ላይ ቀርቦ እንዴት ጦርነት ላይ ለሚገኙ መሪ እንዲህ ትጠይቃቸዋለህ ?!.. ተብሎ ሲጠየቅ 'ሁሉም አሜሪካዊ ቤቱ ሆኖ የሚጠይቀውን ነው የጠየኩት ..ጦርነቱ ዩክሬን እንጂ ዌስት ዊንግ (ዋይት ሃውስ) ውስጥ አይደለም ' ብሎ መልሶ ነበር ።
.
ጉዳዩ ከአምስት ወር በፊትም ዛሬም ዜና ሆኗል ። በርካታ ትልልቅ ሚዲያዎች ተቀባብለው ስርተውታል ። አንዳንድ ጋዜጠኛ ጦርነትህን ሳይሆን አለባበስህን ዜና ያደርገዋል ።
ኤርሚያስ በጋሻው

10 months ago