ተማሪዎችን የባንክ ሂሳብ በማስከፈት በወንጀል የተገኘ ገንዘብን አዘዋውረዋል የተባሉ 9 ግለሰቦች ተከሰሱ
ሁለት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን የባንክ ሂሳብ በማስከፈት በወንጀል የተገኘ ገንዘብን አዘዋውረዋል የተባሉ ዘጠኝ ግለሰቦች ተከሰሱ።
ክሱን የመሰረተዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት ነዉ፡፡
ተከሳሾቹ አቶ ዳዊት አያሌው፣ አቶ ሙየስር አህመድ፣ አቶ ዳንኤል ኪዱ እና አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ጨምሮ ዘጠኝ ግለሰቦች ላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት ክሶችን አቅርቧል።
በአንደኛ ክስ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች የማይገባቸውን ብልጽግና ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከፋይነት እና በመላ ሀሳባቸውና ድርጊታቸው በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ ተካፋይ ሆነዋል።
በዚህም 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑትን 2ኛ እና 3ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ተማሪ ሳሙኤል ምትኩ እና ተማሪ ሳሙኤል አስፈራውን በአንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 500 ብር እንደሚከፈላቸው በመግለጽ በስማቸው የባንክ ሂሳብ እና የሞባይል ባንክ አገልግሎት በማስከፈትና የምስጢር ቁጥር እንዲሰጧቸው አግባብተዋቸዋል።
ተማሪዎቹ የከፈቷቸው የባንክ ሂሳቦች እና የሞባይል ባንክ አገልግሎት ምንም ችግር እንደማያመጣባቸው አሳሳች ቃል በመናገር ምስክሮቹ እምነት እንዲያሳድሩ በማታለል እና የሲም ካርዶችን በመስጠት፣ 2ኛ እና 3ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በአቢሲኒያ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመቅረብ በምስክሮቹ ስም የተከፈቱትን የባንክ ሂሳቦች ቁጥርን እና በሂሳቦቹ ላይ የተመዘገቡትን የሞባይል ባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥሮችን 1 ሺህ 500 ብር በመክፈል ምስክሮቹን አታለው ተቀብለዋል።
ከዚህም በኋላ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮቹን፣ የሞባይል አገልግሎት የተመዘገበባቸውን ሲም ካርዶች እና በሲም ካርዶቹ የተመዘገቡትን የምባይል አገልግሎት የሚስጥር ቁጥሮቹን ለ3ኛ ተከሳሽ በመስጠት፣ 3ኛ ተከሳሽም የባንክ ሂሳብ ቁጥር፣ የሞባይል ባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥር ዮኒ በሚል ስም በከፈተው የዋትስአፕ አካውንት ወደ 4ኛ ተከሳሽ ልኳል።
4ኛ ተከሳሽ ከ1ኛ ዐቃቤ ህግ ምስክር አቶ ሰለሞን ተካ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክተንቀሳቃሽ የሂሳብ ቁጥር ላይ በቼክ የክፍያ ጥያቄ ሲቀርብ ቼኩን ምስክሩ መስጠታቸውን ለማረጋገጥ የሚደወልበትን የሞባይል ስልክ ቁጥር ያልተያዘው አባሪያቸው ወደ ኢትዮ-ቴሌኮም ምስራቅ አዲስ አበባ ዞን ናፑ የፍራንቻይዝ የሽያጭ ቢሮ በመቅረብ በአቶ ሰለሞን ተካ ስም የተዘጋጀ ሀሰተኛ የመንጃ ፈቃድ በማቅረብ ምትክ ሲም ካርድ እንዲወስድ በማድረግ 4ኛ ተከሳሽ ሲም ካርዱን በመቀበል፣ ከ1ኛ ዐቃቤ ሕግ ምስክር አቶ ሰለሞን ተካ የአቢሲኒያ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ላይ ምትክ የሲም ካርዱን በመጠቀም በሞባይል ባንክ አገልግሎት በ2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሳሙኤል ምትኩ ስም ወደ ተከፈተው የአቢሲንያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 99 ሺህ አስተላልፏል።
5ኛ ተከሳሽ አቶ ሰለሞን ተካ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተረከቡት ተንቀሳቃሽ የሂሳብ ቁጥር ላይ ተቀንሶ የሚከፈል ቼክ አቶ ሰለሞን ተካ ጽፈውና ፈርመው የሰጡት በማስመሰል 5ኛ ተከሳሽ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎሮ አደባባይ ቅርንጫፍ ቀርቦ 2 ሚሊየን 650 ሺህ ብር ለክፍያ ሲያቀርብ የቅርንጫፍ ባንኩ ሰራተኞች ቼኩን አቶ ሰለሞን ተካ በትክክል ፈርመው መስጠታቸውን ለማረጋገጥ በሂሳቡ ላይ ወደ ተመዘገበው እና 4ኛ ተከሳሽ ባልተያዘው አባሪው አማካኝነት ምትክ ሲም በማውጣት ይዞት ወደ ነበረው የሞባይል ስልክ ቁጥር ሲደውሉ 4ኛ ተከሳሽ እራሱን የሂሳቡ ባለቤት በማስመሰል ክፍያው እንዲፈጸም ማረጋገጫ ሰጥቷል።
የባንኩ ሰራተኞች የሂሳቡ ባለቤት ማረጋገጫውን እንደሰጡ የወሰዱትን የተሳሳተ እምነት በመጠቀም ቼኩ ተመንዝሮ ወደ 5ኛ ተከሳሽ የንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 2 ሚሊየን 380 ሺህ 729 ብር ከ92 ሳንቲም እንዲተላለፍለት በማድረግ፤ በተማሪዋቹ ስም በተከፈቱ አካዉንቶች የገቡ ገንዘቦችን 3ኛ ተከሳሽ በሞባይል ባንኪንግ ወደ ተለያዩ ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ ቁጥርና የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ ተመዘገቡ የስልክ ቁጥሮች አስተላልፏል።
በአጠቃላይ ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች የማታለል የሙስና ወንጀል ድርጊታቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ከ1ኛ ዐቃቤ ሕግ ምስክር አቶ ሰለሞን ተካ የአብሲኒያ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ላይ 99 ሺህ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 2 ሚሊየን 650 ሺህ ብር በድምሩ 2 ሚሊየን 749 ሺህ ብር ተቀንሶ ወጪ እንዲሆን በማድረግ በፈጸሙት ድርጊት በከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
በ2ኛ ክስ ደግሞ በ2ኛ እንዲሁም ከ6ኛ እስከ 9ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን ተከሳሾች ከላይ በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ከአቶ ሰለሞን ተካ ተንቀሳቃሽ የሂሳብ ቁጥር ላይ 2 ሚሊየን 650 ሺህ ብር ተቀንሶ ወደ 5ኛ ተከሳሽ የንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ከተላለፈ የወንጀል ፍሬ ከሆነ ገንዘብ ላይ ተቀንሶ ወደ ሂሳባቸው የገባውን ገንዘብ ህገ-ወጥ አመጣጥ ለመሰወር ወደ ሌሎች ግለሰቦች በማስተላለፋቸው በፈጸሙት የወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

10 months ago