Logo
Getu Temesgen
ሩሲያ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ የሚደረጉ የስልክ ልውውጦች ላይ በከፊል እገዳ ማስቀመጥ ጀመረች
#ethiopia | ሩሲያ ከውሳኔው ላይ የደረሰችው ሁለቱ መተግበሪያዎች ከማጭበርበር እና ከአሸባሪነት ጋር በተያያዘ ለህግ ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ብላለች።

በዚህ የተነሳ ሩሲያ የወንጀል ተግባራትን ለመቀልበስ በመተግበሪያዎቹ የሚደረጉ አንዳንድ የስልክ ልውውጦች ላይ እገዳ ማስቀመጧ ተዘግቧል።

የሩሲያ የዲጂታል ልማት ሚኒስቴር ቴሌግራም እና ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መተግበሪያቸው ላይ የማጭበርበር እና የሽብርተኝነት ተግባራት እንዳይካሄዱ እንዲያደርጉ ተጠይቀው እምቢ ማለታቸውን ገልፀዋል።

የሩሲያ ባለስልጣናት እነዚህ መተግበሪያዎች ሉዓላዊነታችንን የሚጥሱ ስለሆኑ በሃገራችን አግልግሎት አይስጡ ብለው ሲጠይቁ የነበረ ሲሆን ፕሬዚዳንት ፑቲንም በሩሲያ የበለፀገ እና ከደህንነት ተቋሙ ጋር የተሳሰረ የመልዕክት መለዋወጫ እንዲሰራ ማዘዛቸው ይታወሳል።

ሩሲያ ሁለቱ መተግበሪያዎች መረጃ ከሰጡ እና ከህጓ ጋር ከተስማሙ እገዳው እንደሚነሳ ገልፃለች።

Source: Reuters#tm

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.