አንድ ወቅት በቀን ውስጥ ስንት አገልግል ትሸጫለሽ? ተብላ ተጠየቀች። መልሷ በቀን አንድ በሬና ከዛ በላይ እሸጣለሁ ነበር መልሷ።
የተነሳችበትን ስትናገር እዚህ ለመድረሷ ያሳለፈችውን ውጣ ውረድ ስትመሰክር ማስረጃዋ የእጇ መዳፍ ነበር። ሁሌም የመዳፏን መቆርፈድ ለሕዝብ ታሳያለች። የወየበ የተሸበሸበ የደረቀ የተሰነጣጠቀ የጠቆረ መዳፍ ነው ያላት። የተሸከመችውን የጀሪካን ብዛት የቆላችው የአሻሮ መጠን የሚናገር በምቾት እንኳን አልወዛም ያለ መዳፍ ነው ይዛ የምትዞረው። ጎዳና እስከመውጣት የደረሰች ግን ችግሯን በጥረቷ አሸንፋ ቀና ያለች ብርቱ ሴት ነበረች።
አሁን ባለፈው ትልቅ ሆቴል ከፍታ እንግዶችን ጋብዛ አስመርቃም ነበር።
ምን አይነት ክፉ ማዕበል እንዳናወጣት እንጃ በቀን አንድ በሬ ሙሉ ሰርታ የምትሸጠው ቲጂ አገልግል ዛሬ እንደራባት ማደሪያ እንዳጣች ሰዎች እያሰቃዩዋት እንደሆነ እንደእብድ እየሆነች ስትናገር አየዋት!
አንዳድ ሰው ከወደክበት ያነሳል አንዳንድ ሰው ከተነሳህበት ጎትቶ ይጥላል።እንባዋ ቁጭቷ በተቸገረች ጊዜ ሰው ማጣቷን ስትናገር አንጀት ትበላለች።
ትናንት ባለትልቅ ሆቴል ዛሬ ማደሪያ አጥቶ እስከመለመን መድረስ ምን አይነት ጉድ ነው የወረደባት ያስብላል።
እግዚአብሔር ይድረስልሽ እኔስ አሳዝነሽኛል
via Eden Liul

10 months ago