Logo
ጌች ሐበሻ
ጋዜጣዊ መግለጫ

ከ "ሩጫም በላይ" በሚል መርሃግብር ግራንድ አፍሪካ ራን 10 የበጎ አድራጎት አጋር ድርጅቶቹን አስተዋወቀ።

ዋሽንግተን ዲሲ (ነሐሴ 9/2017) በዚህ አመት ከግራንድ አፍሪካ ራን ጋር በአጋርነት የሚሰሩ 10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ሆነዋል

"አብሮነት መሻል ነው" በሚል መሪ ቃል የሚከናወነው አመታዊው የግራንድ አፍሪካን ራን ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ በመጪው ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ይካሄዳል

ግራንድ አፍሪካን ራን "ከሩጫ በላይ" በሚል ሀሳብ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ውስጥ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የማህበረሰባችን ክፍሎችን ከሚደግፉ የበጎ አድራጎት አጋሮች ጋር በየአመቱ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ዘንድሮም ከ10 የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት ተዘጋጅቷል። አጋሮቹ በኦቲዝም፣ በአካል ጉዳት፣ በካንሰር፣ በልብ ህመም፣ በትምህርት፣ በድህነት ማስወገድ እና በሴቶች ልጆች ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ናቸው

እነዚህ የበጎ አድራጎት አጋሮች Heart Attack Ethiopia (HAE), The Belisha Foundation (TBF), Wegene Ethiopian Foundation (WEF), Girls Gotta Run Foundation (GGRF), Alpha Breast Cancer Support Service (ABCSS), African Women’s Cancer Awareness Association (AWCAA), Ethiopian Eritrean Special Needs Community (EESNC), Raeye Children Aid (RCA), Your Ethiopian Professionals Network (YEP), and SPOT ናቸው፡።

የእያንዳንዱ የበጎ አድራጎት አጋር ተወካይ ማህበረሰባችን በዝግጅቱ እንዲሳተፍ ጥሪ በማቅረብ ለመረጡት የበጎ አድራጎት እገዛ በማድረግ ለተሳትፏቸዉ የበለጠ ትርጉም እንዲሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ጠይቀዋል። ተሳታፊዎች ከጓደኞቻቸው፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ከጎረቤቶቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የኢሜይል፣ የአጭር ጽሑፍ መልእክት፣ የስልክ ጥሪ፣ የአካል እና የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን በመጠቀም ለመረጡት የበጎ አድራጎት ተቋም ገቢ እንዲያሰባስቡም መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዘጋጆቹ በበኩላቸው ተሳታፊዎች የ5ቱን ኪሎ ሜትር ርቀት በ1ሜትር፣ 10 ሜትር ወይም በ1 ኪሎ ሜትር በመከፋፈል ለመደቡት ርቀት ወዳጅ ዘመድ ጓደኛቸው የመረጡትን በጎ አድራጎት እንዲደግፉ በማድረግ ገቢ ሲያሰባስቡ ድጋፋቸው በቀጥታ ወደ በጎ አድራጎት ድርጅቱ ገቢ እንደሚሆን አስታውቀዋል። እነማን ምን ያህል እንደደገፉም በገቢ ማሰባሰቢያዉ ድረ ገፅ ላይ መከታተል እንደሚቻል ጠቁመዋል። ዝግጅቱ የማህበረሰብ ግንኙነትን በማጠናከር እያንዳንዱ እርምጃ ለበጎ አድራጎት እንዲዉል መንገዱን ያመቻቻል ብለዋል።

በምዕራቡ ዓለም በስፋት እና ለረጅም ጊዜ በተለመደዉ አሰራር የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሩጫ ዝግጅቶችን በመጠቀም ገቢ የሚያሰባስቡ ሲሆን ዛሬ በይፋ የተዋወቁት 10ሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ግራንድ አፍሪካ ራንን እንደመድረክ በመጠቀም ተሳታፊዎች በአቅራቢያቸዉ ባለ ወዳጅ ዘመድ ጓደኛ ቤተሰብ በኩል ለመረጡት በጎ አድራጎት ድርጅት ገቢ እንዲያሰባስቡ አጋር ድርጅቶቹና አዘጋጆቹ በጋዜጣዊ መግለጫው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል

ለተጨማሪ መረጃ ይጎብኙ፡ https://www.africanrun.com...

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.