ካለን ብናካፍል - በጎንደር
#ethiopia | ከሰሞኑን ጎንደር ከተማ ለስራ ባቀናንበት ወቅት ወጣት ዳዊት አየነው የ‘ካለን ብናካፍል’ የህጻናት፣ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አገኘነው ማዕከሉ ስለሚሰጠው አገልግሎት የተወሰነ ጉዳዮችን አጫውቶናል።
የማዕከሉ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወጣት ዳዊት አየነው በርከት ላለ ጊዚያት በመቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከል እና በአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
በበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት በመስጠት ከቆየ በኃላ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ብዙ ጊዜ መቀመጫውን እንደ አዲስ አበባ እና መሠል ትላልቅ ከተሞች ላይ ብቻ መሰረት ማድረጋቸውን በመመልከት በገጠር እና በወረዳ እንዲሁም በአነስተኛ ከተሞች ለሚገኙ ወገኖች ተደራሽነት እንደማይፈጥር በመገንዘብ ጎንደር ከተማ ላይ በራሱ አቅም በ2010 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የበጎ አድራጎት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አጫወተን በሂደትም ህክምናቸውን ተከታትለው የሚመለሱ ትራንስፖርት በመስጠት ፣ ጧሪ ደጋፊ የሌላቸውን አዛውንቶችን በመደገፍ እንዲሁም በአደገኛ ሱሶች የተጠቁ ወገኖችን የሚረዳ ማዕከል ወደ ማቋቋም መሠረተ።
የማዕከሉ ስም የሆነው 'ካለን ብናካፍል' የሚለው አስተሳሰብ የተመሰረተው፣ ማንም ሰው ከጊዜው፣ ከጉልበቱ፣ ከእውቀቱ፣ ከሀሳቡ ወይም ከሀብቱ ሊኖረው ስለሚችል፣ እነዚህን ለሌሎች በማካፈል ብዙዎችን መደገፍ እንደሚቻል በማሰብ መመረጡን ወጣት ዳዊት ይናገራል።
🔹 ማዕከሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
◈ የመጠለያ፣ የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ፦ ማዕከሉ በቋሚነት ከ500 በላይ ለሆኑ ጧሪ የሌላቸው ወገኖች መጠለያ፣ ምግብ፣ አልባሳት እና የቤተሰብ እንክብካቤ ያቀርባል። እነዚህ ወገኖች እድሜያቸው ከጨቅላ ህፃናት እስከ 80 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ናቸው።
◈ የህክምና አገልግሎት፦ አረጋውያን እና የአእምሮ ህመምተኞች የህክምና ድጋፍ እንዲያገኙ ያግዛል።
◈ የትምህርት እና የስልጠና ድጋፍ፦ እናቶቻቸው በአእምሮ ህመም ምክንያት ከነጨቅላዎቻቸው ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ህፃናት እዚያው እንዲማሩ እና ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል።
◈ ቤት ለቤት ድጋፍ፦ ከ700 ለሚበልጡ ወገኖች በየቤታቸው ድረስ በመሄድ የድጋፍ አገልግሎት ያደርጋል።
የማዕከሉ ተግዳሮቶች እና ስኬቶች
🔹ተግዳሮቶች፦
▫️ገንዘብ እና የድጋፍ መቆራረጥ፦ ማዕከሉ የሚተዳደረው በውጪ ድርጅቶች ወይም ስፖንሰርሺፕ ሳይሆን፣ በበጎ ፍቃደኞች በሚደረግ ድጋፍ ብቻ በመሆኑ የድጋፍ መቆራረጥ ያጋጥማል።
▫️የትራንስፖርት ችግር፦ ታማሚዎችን ወደ ሆስፒታል፣ እንዲሁም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ወገኖችን ወደ ቀብር ቦታ ለማድረስ የትራንስፖርት እጥረት አለ።
▫️የሚዲያ ተደራሽነት፦ ማዕከሉ ከአዲስ አበባ በ700 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የሚዲያ ሽፋን ማግኘት አስቸጋሪ ነው።
🔹ስኬቶች፦
🔸የጎንደር ከተማ አስተዳደር የማዕከሉን ስራ አይቶና ገምግሞ 3.5 ሄክታር መሬት መስጠቱ።
🔸 ኢትዮ ቴሌኮም የማዕከሉን የአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) አገልግሎት በጎ ፈቃድ ማበርከቱ።
🔸 በ8183 ላይ ለአጭር የጽሁፍ መልዕክት ድጋፍ አገልግሎት እድል ማመቻቸቱ።
🔸 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ከማዕከሉ ጋር በጋራ መስራቱ።
🔹 ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ወገኖች
ለማዕከሉ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ በጎ ፈቃደኛ ወገኖች፣ ድጋፋቸውን ማድረስ የሚችሉባቸው መንገዶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦
1. በአካል በመገኘት፦
📌አድራሻ 1፡ ጎንደር ከተማ፣ ሽዋ ዳቦ፣ ቀበሌ 18።
📌 አድራሻ 2፡ ጎንደር ከተማ አዘዞ አየር ማረፊያ ወደ ቆላድባ በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከ2.5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ።
📌 በቅርቡም አዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ማስተባበሪያ ቢሮ ለመክፈት በእንቅስቃሴ ላይ ነው።
2. በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ
► የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት፡ 8183
► በኢትዮ ቴሌኮም አጭር መልእክት፡ 8183 ብለው OK ብለው መላክ ይችላሉ።
► በቴሌ ብር፡ በቴሌ ብር 'Fundraising' ገጽ ውስጥ በመግባት 'ካለን ብናካፍል' የሚለውን በመምረጥ መደገፍ ይቻላል።
3. በስልክ ቁጥር፦
☎️ 0941-02-03-04
☎️ 0987-02-03-04
4. በማህበራዊ ሚዲያ፦
◍ Facebook፡ ካለን ብናካፍል
◍ Telegram፡ https://t.me/dave13222
◍ TikTok፡ https://www.tiktok.com/@ka...

10 months ago