Logo
YenetaTube
"የተወሰነውን ግዛት ለዩክሬን ለማስመለስ እንሞክራለን" አሉ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አርብ ዕለት ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሚያደርጉት ውይይት ለዩክሬን የተወሰነ ግዛት ለማስመለስ እንደሚሞክሩ ተናገሩ።

በዋይት ሐውስ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት "ሩሲያ የዩክሬንን ሰፊ ክፍል ይዛለች።ዋና ግዛት ነው የያዘችው።የተወሰነውን ግዛት ለዩክሬን ለማስመለስ እንሞክራለን" ብለዋል።

ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት በሳምንቱ መጨረሻ በአላስካ ተገናኝቶ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።

ትራምፕ ከፑቲን ጋር ከተገናኙ በኋላ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለውጥ ይኖር እንደሆነ ማወቅ እንደሚችሉ ተናግረዋል እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

የአርብ ዕለቱ ስብሰባ ፑቲን ጦርነቱን እንዲያቆም ለማበረታታት ያለመ እና "አቋሙን ለማወቅ የሚደረግ ስብሰባ" እንደሚሆን ገልፀው፣ ይህንን ጉባዔ እንደ መነሻ እንደሚመለከቱት ተናግረዋል።

አላስካ የሚደረገው የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ ከተሰማ በኋላ ዜሌንስኪ የኪየቭ ግብዓት የሌለበት ማንኛውም ስምምነት "የከሸፈ ውሳኔ" ይሆናል ብለዋል።

ክሬምሊን በተደጋጋሚ ከዜሌንስኪ ጋር የፊት ለፊት ውይይት ሊኖር እንደማይችል ተናግሯል።

በቅርቡ ፕሬዚዳንት ፑቲን ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ጊዜው ሩቅ ነው ብለው ነበር።

ዜሌንስኪ ረቡዕ ዕለት ከትራምፕ፣ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና ከአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ጋር በቪዲዮ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ETHIO FM

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.