Logo
FIDEL POST NEWS
የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የ2018 ዓ/ም የትምህርት የጊዜ ሰሌዳን ለክልል ትምህርት ቢሮዎች አሳውቋል።

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተገኘው መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር በላከው የዓመቱ የትምህርት ካላደር ፦

- እስከ ነሐሴ 30/2017 ዓ/ም የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ይካሄዳል።

- መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት የሚያደርጉበት ጊዜ ነሐሴ 19/2017 ዓ/ም ነው።

- መስከረም 5/2018 ዓ/ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ (day one class one) የሚጀምርበት ቀን ነው።

- ከጥር 18 እስከ ጥር 22 / 2018 ዓ/ም የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ነው። ከጥር 25 እስከ 29 ትምህርት ቤቶች ዝግ ይሆናሉ።

- የካቲት 2/2018 ዓ/ም የሁለተኛ ሴሚስተር መደበኛ ትምህርት ይጀምራል።

- ከሰኔ 1 እስከ 5/2018 ዓ/ም የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ይሰጣል።

- ከሰኔ 8 እስከ 12/2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ይሰጣል።

- የሁለተኛ ሴሚስተር ፈተና ከሰኔ 15 እስከ 19/2018 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

- የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 26/2018 ዓ/ም ድረስ ለመስጠት ታቅዷል።

(የ2018 ዓ/ም የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ)
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.