Logo
ጌች ሐበሻ
"የወዲያነሽ" መጽሐፍ ዳግም ታትሞ ለንባብ በቃ

በአንጋፋው መምህርና ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል በ1978 ዓ.ም ተጽፎ ለንባብ የበቃው እና በርካታ አንባቢዎችን ያፈራው “የወዲያነሽ” የተሰኘው የረጅም ልብ ወለድ መጽሐፍ፣ ዳግም ታትሞ ለአምስተኛ ጊዜ ለህትመት ቀርቧል።

መጽሐፉ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በተካሄደ ልዩ መርሐግብር ተመርቋል።

መጽሐፉ ቀደም ሲል በሳንሱር ምክንያት ያልገቡ አንዳንድ ሐረጎችና አንቀጾች የተካተቱበት ሲሆን አንዳንድ አርትዖት መደረጉን በምረቃው መርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።

በመጽሐፍ ምርቃት መርሐግብር ላይ ደራሲያን የተለያዩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የደራሲው ቤተሰቦች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

📷 አቤል ምህረቴ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.