Logo
SeledaPost
በሳምንት 6 እንቁላል መብላት እድሜን በአንድ ሶስተኛ ያራዝማል _ጥናት

የሳይንስ ሊቃውንት በመደበኛነት እንቁላል መመገብ ያለዕድሜ የመሞትን አደጋ በ30% ይቀንሳል እንደሚቀንስ በጥናታችን አረጋግጠናል ብለዋል።

በሳምንት ቢያንስ 6 እንቁላሎችን ከበሉ፣ እድሜዎን በአንድ በሶስተኛ ማራዘም ይችላሉ። ይህም ለአንጎል፣ ለልብ እና ለጡንቻዎች የሚሆን ኃይለኛ የፕሮቲን መጠን፣ በተጨማሪም ቫይታሚን ቢ12፣ ኤ፣ ዲ እና ኬ2 ስላሉት ነው። እንቁላል ሜታቦሊዝምን ያፋጥናል፣ ኮሌስትሮልን ያስተካክላል እንዲሁም የልብና የደም ዝውውር በሽታዎች የሚያስከትሉትን አደጋ በ20% ይቀንሳል ይላል ጥናቱ።

በጆርናል ኒዩተረንትስ ላይ በታተመው ጥናት ተመራማሪዎች እንዳገኙት በአንጻራዊ ሁኔታ ጤነኛ ለሆኑ አረጋውያን በሳምንት ከ1-6 እንቁላሎችን መመገብ፣ እንቁላል አልፎ አልፎ ወይም በጭራሽ ከማይመገቡት ጋር ሲነፃፀር በሁሉም ምክንያት ለሚከሰት ሞት የልብና የደም ዝውውር ምክንያት ለሚከሰት ሞት የመጋለጥ እድሉ ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል።

የሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና እና መከላከያ ሕክምና ትምህርት ቤት የፒኤችዲ ተማሪ እና መምህር የሆኑት ሆሊ ዋይልድ እንዳሉት፣ እንቁላል በጭራሽ ወይም አልፎ አልፎ ከሚመገቡ አረጋውያን (በወር እስከ ሁለት ጊዜ) ጋር ሲነፃፀር፣ በሳምንት ከ1-6 እንቁላሎችን የበሉ አረጋውያን ከማንኛውም ምክንያት ለሚከሰት ሞት የመጋለጥ እድላቸው 15 በመቶ ያነሰ ሲሆን፣ ከልብና የደም ዝውውር ስርዓት በሽታዎች ጋር በተያያዘ ለሚከሰት ሞት የመጋለጥ እድላቸው ደግሞ 29 በመቶ ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል።

Seledadotio
Seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.