"ጥበብ ቅንነትን ትወዳለች"ድምጻዊ አቤል ሙሉጌታ
#ethiopia I ድምጻዊው ይህንን ያለው አራተኛ የሙዚቃ ስራውን ወይም "ቅን" የተሰኘው የሙዚቃ አልበሙን ባስተዋወቀበት መድረክ ነው።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ በርካታ ስራዎችን በመስራት ከ90ዎቹ አንስቶ እጅግ ተወዳጅነትና ተቀባይነትን ያገኘው ድምጻዊ የዜማና የግጥም ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ኛ አልበሙን አጠናቆ ለአድማጮች አድርሷል።
በ1999 "አላማሽም"በ2003 "ተገርሜ"
በ2011"እንነጋገር" በተሰኙ የሙዚቃ አልበሞቹ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትና ተወዳጅነት አትርፎባቸዋል።
የድምጻዊ አቤል ሙሉጌታ 4ኛ አልበም "ቅን" አስራ አራት ትራኮች ያያዘ ሲሆን ግጥምና ዜማ እራሱ አቤል ሙሉጌታ ሰርቷቸዋል።
በቅንብሩ በኩል ካሙዙ ካሳ፣ አቤል ጳውሎስ፣ ታምሩ አማረ፣ አዲስ ፍቃዱ፣ ሮቤል እንዳለ፣ አብርሀም ኪዳኔና ሙሳ ማቲ ተሳትፈዋል።
በሚኪሲንግ ሰለሞን አማረ፣ አቤል ጳውሎስና አብርሀም ኪዳኔ በማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል ነው የተባለው።
በርካታ የሀገራችን የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያሳተፈው የአቤል ሙሉጌታ ቅን የተሰኝው አልበም ዛሬ ሀምሌ 11 ቀን 2017 አመት በራሱ የአቤል ሙሉጌታ የዩቱዩብ ቻናል ይለቀቃል ተብሏል።
ድምጻዊ አቤል ሙሉጌታ "ቅን" ሰርቶ ለአድማጮች ለማቅረብ አምስት አመት እንደፈጀበት ተናግሯል።
በወጪ በኩል አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 5ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተነግሯል።
በዚህ አልበም ከ40 በላይ የሙዚቃ ሰዎች እንደተሳተፊበት የገለጸው አቤል ሙሉጌታ በአልበሙ የቅኝት ስራዎች እንደሰራ ተናግሮ ስራዎቹም በራሱ ቅኝት እንደተጫወታቸው ተናግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

1 year ago