Logo
YenetaTube
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ በርካታ ስራዎችን በመስራት ከ90ዎቹ መጨረሻ አንስቶ እጅግ ተወዳጅነትና ተቀባይነትን ያገኘው ድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ አልበሙን ለማውጣት ዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።

በ1999 "አላማሽም" በ2003 "ተገርሜ" በ2011 "እንነጋገር" በተሰኙት የሙዚቃ አልበሞቹ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትና ተቀባይነት ያገኘው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ለበርካታ የሀገራችን አንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን ማለትም ፀሃዬ ዮሃንስ፣ዳዊት ፅጌ፣ብዙአየሁ ደምሴ፣ሄለን በርሄ፤ቬሮኒካ አዳነ፣ራሄል ጌቱ፣ተመስገን ገ/እግዚአብሔር፣መስፍን(ነይ በክረምት)ን ጨምሮ ለሌሎች በርካታ ድምፃውያን ተወዳጅ የሆኑ የግጥምና ዜማ ስራዎችን ሰርቷል።
የድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ አልበም 14 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅም 5 ዓመታትን ወስዷል። የሁሉም ትራኮች ግጥምና ዜማ በራሱ በድምፃዊው በአቤል ሙሉጌታ ሲሰሩ በቅንብር ካሙዙ ካሳ፣አቤል ጳውሎስ፣ታምሩ አማረ፣አዲስ ፍቃዱ፣ሮቤል እንዳለ፣አብርሃም ኪዳኔና ሙሳ ማቲ በሚክሲንግ ሰለምን ሃ/ማርያም፣አቤል ጳውሎስና አብርሃም ኪዳኔ በማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል። ይህ በርካታ የሀገራችን የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያሳተፈውና የሀገራዊ፣የማህበራዊ፣የፍቅር፣የፍልስፍናና ታሪካዊ ጉዳዮችን የሚያነሳው የሙዚቃ አልበም የፊታችን ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም በዕለተ ዓርብ ለአድማጮች በራሱ የአቤል ሙሉጌታ የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.