Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#ethiopia
#usa

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያዩ።

ውይይቱ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ እንደነበርና እጅግ ፍሬያማ እንደሆነ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

" ያካሄድነው ውይይት በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን እድሜ ጠገብ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ በሁለቱም አገራት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው " ብለዋል።

በውይይቱ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በተመለከተ ማረጋገጫ መስጠቷን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

" የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊና ባለብዙ ወገን መድረኮች ቅድሚያ በምንሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ አብረን ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጣለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia #ethiopia #israel ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ውጤታማ እና ፍሬያማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። " በሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በጋራ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በጋራ በሆኑ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጠናል " ሲሉ አስታውቀዋል። ጥቅምት 2 ቀን…
12 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.