Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት

ከነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2019 ዓም በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከትላንት ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ የሆነ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለሁለት ወራት ማለትም ከነሐሴ 1 - መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ይታወቃል።

ፍ/ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምረው ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች ቀጥለው ቆይተዋል።

በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት ፍርድ ቤቶች ከትላንትና ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት ጀምረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.