🤩ወጣት ዮርዳኖስ አምበሉ🤩
የአካውንቲንግ የማዕረግ ተመራቂዋና በስራ ላይ የተሰማራችው ዮርዳኖስ አምበሉ የተባለች ወጣት በአዲስ አበባ ከተማ ወመዘክር እያለች ምሽት ላይ " በስለት ተወግታ " ተገድላለች።
ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠረው አብሯት ይሰራ የነበረና የፍቅር ጥያቄ አቅርቦ ያልተቀበለችው ግለሰብ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሟቿ ላይ ስለተፈጸመው ትክክለኛ ነገር የቅርብ ቤተሰቦቿን አነጋግረናል።
ጠበቃና የሕግ ባለሙያ የሟቿ የቅርብ ቤተሰብ አቶ በርታ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
ወጣት ዮርዳኖስ ባለፈው ሳምንት ወመዘክር ግቢ ውስጥ ምሽት ላይ በስለት ተወግታ ሕይወቷ ማለፉን ገልጸዋል።
" አስከሬኗን አይቻለሁ። በመጀመሪያ ከጀርባ ሽንጧ ላይ ነው የወጋት፤ ልትከላከል ዞር ስትል ቦርሳዋ ሁሉ ተወግቷል " ሲሉም እማኝነታቸውን ሰጥተውናል።
" ስድስት፣ ሰባት ቦታዎች ላይ ነው በስለት የተወጋችው። አንገቷ፣ ጡቷ፣ እግሯ፣ ደረቶቿ ላይ ተወግታለች " ብለዋል።
" በጩቤ ነው የወጋት ጩቤው ጽድ ውስጥ ጥሎት ተገኝቶ በኤግዚቢትነት ተይዟል። አዲስ ጩቤ ገዝቶ ነው፤ መሸፈኛ ሁሉ አለው። ወመዘክር ግቢ የደረጃው በር ላይ ነው የወደቀችው። ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ዛሬ ራሱ ሄጄ ነበር ደሟን ሁሉ አይቸዋለሁ " ነው ያሉት።
" ዛሬ ወመዘክር ሄጄ ነበር ለአንዳንድ ጉዳይ፥ የወመዘክር ካሜራ በሩ ላይ ስትወድቅ የሚያሳየው ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ አካባቢ ነው " ሲሉ ዛሬ የተነገራቸውን መረጃ ተናግረዋል።
ሟች ከመገደሏ በፊት ምን ብላ ነበር?
እኚሁ ቤተሰብ፦
" ዮርዳኖስ በተገደለችበት ምሽት 1 ሰዓት 30 ደቂቃ ገደማ 'ዛሬ ሙዴ መጥቷል፤ ወመዘክር ነኝ። አጠናለሁ፤ አመሻለሁ፤ በራይድ እመጣለሁ' ብላ ለእህቷ የፅሑፍ መልዕክት ልካለች።
ከምሽት 3 ሰዓት 30 ደቂቃ ጀምሮ ግን እኔም ባለቤቴም ስንደውል ስልኳ አይነሳም። 5 ሰዓት አካባቢ ተነሳ። ግን ፖሊስ ነው ለካ ያነሳው።
ፖሊስ መሆኑን በኋላ ላይ ነው ያወቅሁት ስልኩን አንስቶ 'ማነህ?' ሲለኝ ወንድሟ ነኝ አልኩኝ፤ ልመጣ ነበር 'ወመዘክር ላይብራሪ ነኝ' ብላ አመሸችብን አልኩ፤ 'ስልኳ ወድቆ አግኝተን ነው' ተባልኩ።
እየሮጥኩ ሄድኩ፤ ስደርስ ግን ዮርዳኖስ ተገድላለች " ሲሉ አስረድተዋል።
" ፖሊስ 'የምትጠረጥሩት ቤተሰብ፣ ጠላት አላችሁ ወይ?' " እንዳላቸው፣ እሳቸውም " የምንጠጥረው የለም፤ ምክንያቱም ሰላማዊ ቤተሰብ ነን። ግን የሆነ ልጅ 'በአንቺ ሕይወት በጣም እቀናለሁ' ብሏት ቤተክርስቲያን ትወስደው ነበር። በኋላ ሁኔታውን ወደ ፍቅር ቀይሮ 'እሺ ካላልሽኝ ራሴን አጠፋለሁ' ይል ነበር። ከዚህ የዘለለ ጓደኛም የላትም " ብለው እንዳስረዱም ነግረውናል።
👉 ከተጠርጣሪ ወደ ሟች ቤተሰብ የተደወለው ስልክ ነገር
የዮርዳኖስን አስከሬን ከጳውሎስ ሆስፒታል ይዘው እየወጡ እያለ ከተጠርጣሪ ቤተሰብ ስልክ ተደውሎ ጉዳዩ "በሽምግልና" እንዲያዝ መጠየቃቸውን ጠበቃ በርታ ነግረውናል።
የተባሉትን ሲያስረዱ፦
" ለካ በግድያ ተጠርጣሪው 'ሰው በስለት ወግቻለሁ' ብሎ ለአባቱ ተናግሯል። የተጠርጣሪ አባት በባለቤቴ ስልክ ደውሎ 'የሆነው ነገር ምንድን ነው ? እባክህ አስረዳኝ' ሲለኝ ማነህ? ዘመድ ነህ? አልኩት።
'አይ ዘመዳማ እናንተ ናችሁ' አለኝ፤ ከዛ እንደ ሕግ ባለሙያ ነገሮችን ማሰብ ጀመርኩና ድምጹን ላውድ አድርጌ ጓደኞቼ ንግግሩን መቅዳት ጀመሩ። 'ሞታለች ወይ?' ሲለኝ የሚነግረኝ ለመረጃ ይጠቅማል በሚል 'አልሞተችም' አልኩት።
አባትዮው ግራ ተጋብተዋል ጉዳዩ 'በሽምግልና ይያዝ፤ ልጄ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ነው' አሉኝ። የድምፅ ማስረጃውን ያዝኩ። ትሩኮለር ላይ ስም ስንፈልግ እንዳለ ረጋሳ ይላል የተደወለበት ስልክ፤ ተጠርጣሪው ኢዮብ እንዳለ ነው ስሙ።
በኋላ ቢሮ አብረውት የሚሰሩ ልጆችን የተጠጣሪውን ስም ከነአያቱ ፈልጉልኝ አልኩ። ስሙም ኢዮብ እንዳለ ረጋሳ ሆነ" ብለዋል።
" ተጠርጣሪው የፍቅር ጓደኛዋ አይደለም " ያሉት የሟች ቤተሰብ፣ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ስትከለክለው "ይከታተላት" እንደነበር ገልጸዋል።
"በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው 'ፍቅረኛዋ ነው' መባሉ ውሸት ነው። ፍቅረኛዋ አይደለም 'እምቢ' ስላለችው ነው የገደላት" ብለዋል።
"ተጠርጣሪው ቤተክርስቲያን አካባቢ 'በፍቅር የጠየኳት ልጅ እምቢ ብላኛለች፤ ፀልዩልኝ እንቅልፍ አልተኛም ስለማለቱ ማስረጃዎች አሉን" ነው ያሉት።
ስለሟችና ተጠርጣሪ ግንኙነት አቶ በርታ ምን አሉን?
" ሟቿና ተጠርጣሪው አንድ ቢሮ ውስጥ ይሰሩ ነበር። ዮርዳኖስ በጣም ጎበዝ ልጅ ነበረች። የማዕረግ ተመራቂ ነች ስራም በተመረቀችበት ይዛ ነበር።
እየሰራች እያለች ልጁ ይተዋወቃታል።
'ግን ምንድን ነው እንደዚህ ያረጋጋሽ ነገር? በጣም ብዙ ነገር ላይ ኮንፊደስሽ፣ ስርዓትሽ?....ይላታል። እሷም 'እኔ በእምነቴ ጠንካራ ነኝ' ስትለው፥ 'አንቺ የምትሄጅበት ቦታ መሄድ እፈልጋለሁ' ይላታል። ይህን ሁሉ እንደቤተሰብ ትነግረናለች።
ይዘሽው ሂጂ ምን ችግር አለው አልናት፤ ቤተክርስቲያን ይዛውም ትሄድ ነበር። ስለልጁም ነግራናለች፤ ሜዲሲን ይማር ነበር፤ ከዚያ በኋላ ነው አካውቲንግ ተምሮ እነዮርዳኖስ ጋር ሲሰራ የነበረው።
ይህ በእንዲህ እያለ አንድ እለት በባለቤቴ ስልክ ሌሊት 6 ሰዓት ተደወለ።
ባለቤቴ ስታነሳው 'ዮርዳኖስ አለች?' አለ፤ ባለቤቴ ተናዳ 'ምን የሚሉት ብልግና ነው፤ እንዴት በዚህ ሰዓት ይደወላል?' ብላ ስልክ ዘጋች።
ተደውሎ ተፈልጋ እንደነበር ጠዋት ለዮርዳኖስ ነግርናት፤ ስልኩንም ስንነግራት 'ያ ባለፈው የነገርኳችሁ 'ቸርች ውሰጅኝ ሲለኝ የነበረ ልጅ በኋላ ላይ ተቀይሮ 'አፈቅርሻለሁ' አለኝ፤ ሲያስቸግረኝ ስልኩን ብሎክ አደረኩኝ። ባንቺ ከደወለማ ብልግና ነው ራሴ ጉዳዩን Handle አደርጋለሁ' አለች።
'እምቢ' ብላዋለች፤ ምንም ግንኙነት የላቸውም። አላማየን ላሳካ የምትል ልጅ ነች፣ ምልልሷ ቢሮ፣ ወመዘክር እና አብርሆት ላይቦረሪ ነው። እዛ ድረስ ያለውን እናውቃለን " ብለዋል።
ዮርዳኖስ በአካውንቲንግ የማዕረግ ተመርቃ በስራ የተሰማራች፤ የACCA ትምህርቷን ለማጠናቀቅ ሁለት ኮርሶች ብቻ የቀሯት ጎበዝና ፈጣን የ23 ዓመት ወጣት እንደነበረች ገልጸዋል።
የሟች ቤተሰቦች ስጋትና መልዕክት ምንድን ነው ?
የሟች እህት ወ/ሮ ለምለም አምበሉ፣ " አገራችን ወዴት እየሄደች እንደሆነ ራሱ ግራ እየገባኝ ነው " በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" እንዲህ አይነት ጉድ ማንም ላይ አይድረስ፤ ይህን ነው የምለው ሌላ ምንም አቅም የለኝም " ሲሉ እምባ እየተናነቃቸው ገልጸዋል።
ጠበቃ በርታ፣ " የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችን እንደሚያውቅ ሰው ፍርድ ቤትን እፈራለሁ፤ ፍርዱ በጣም ይዘገያል፤ ሲዘገይ ነገሮች ይበላሻሉ፤ የዘገዬ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል " ብለዋል።
" ዮርዳኖስ ያሳደገቻቸው ሴት ልጆች አሉኝ። እዚህ አገር ላይ ልጆቼን ማሳደግ እየፈራሁ ነው። አስተማሪ ቅጣት ካልተሰጠ በስተቀር ማንም እየተነሳ ልጆች ይገደላሉ። ዮርዳኖስ 'አልፈልግም' ስላለች ነው የተገደለችው። ልጆቻችን ሀሳባቸውን መግለጽ የማይችሉበት ደረጃ እየደረስን ነው " ብለዋል።
" ዮርዳኖስ ላይ ክትትል ሲያደርግባት እንደነበር ጓደኟቿ ናቸው በኋላ የነገሩን፤ እሷ ብትነግረን የሆነ ነገር እናደርግ ነበር " ሲሉም ሌሎቹን አስጠንቅቀዋል።
ተጠርጣሪው መያዙን ገልጸው፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮማንደር አበበ እና ኢንስፔክተር ዮሐንስን አመስግነዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

1 day ago