Logo
TIKVAH-SPORT
ሉሲዎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል !

የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ያደረገውን የኦሎምፒክ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ 1ለ1 አጠናቋል።

የሉሲዎቹን ግብ መሳይ ተመስገን ከመረብ ማሳረፍ ችላለች።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሩዋንዳን በድምር ውጤት 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ሶስተኛው ዙር አልፋለች።

የኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድን የሶስተኛ ዙር ጨዋታውን ከታንዛኒያ አቻው ጋር ያደርጋል።

ታንዛኒያ ከቦትስዋና ጋር ያደረገችውን ጨዋታ በድምር ውጤት 7ለ0 አሸንፋ ለሶስተኛው ዙር ማለፍ ችላለች።

የሴቶች ኦሎምፒክ የማጣሪያ ውድድር ከዚህ በኋላ ሶስት ዙሮች የሚቀሩት ይሆናል።

በ ሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ላይ አፍሪካን በመወከል #ሁለት ሀገራት ብቻ ተሳታፊ ይሆናሉ።

@tikvahethsport      kidusyoftahe
11 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.