የመድኃኒት እጥረት ለታካሚዎች ፈተና እንደሆነበት የአዶላ ወዩ ሆስፒታል አስታወቀ
ታካሚዎች በሚፈልጉት ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት ማግኘት አለመቻላቸው በጤና ተቋማት ከሚነሱ ቅሬታዎች መካከል አንዱ ሲሆን በአዶላ ወዩ ጠቅላላ ሆስፒታል አልፎ አልፎ የመድኃኒት እጥረት እንደሚያጋጥም ተገልጿል፡፡
በሆስፒታሉ ከሚታከሙ ታካሚዎች ከሚነሱ ቅሬታዎች መካከል በቂ መድኃኒት አለመኖርና የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት በሚፈልጉት ጊዜ ማግኘት አለመቻል ዋነኞቹ መሆናቸው ተጠቁሟል። ይህም ታካሚዎች ከሆስፒታሉ ውጭ መድኃኒት ለመፈለግ እንዲገደዱና ተጨማሪ ወጪ እንዲያወጡ ሊያደርግ የሚችል ችግር ነው ተብሏል፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ኑሮ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት የመድኃኒት እጥረቱ ቋሚና በተከታታይ የሚያጋጥም ችግር ባይሆንም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡በሆስፒታሉ የመድኃኒት አቅርቦቱን ለማሻሻልና የታካሚዎችን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለማሟላት ከዞኑ ጤና ቢሮና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሠራ ይገኛል።
በዚህም በታካሚዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቀነስና የህክምና አገልግሎቱ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀጥል የተለያዩ የትብብር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ መሀመድ ኑሮ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

3 hours ago