Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያ በአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ ለመሳተፍ ታይላንድ ባንኮክ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ከስብሰባው ጎን ለጎን ውይይቶችን ማድረግ የጀመረ ሲሆን ስብሰባው ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት፣ ከልማት አጋሮች እና ከፖሊሲ አውጪዎች ጋር ኢትዮጵያ ቅድሚያ በምትሰጣቸው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመምከር፣ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ለማጠናከር የሚያግዝ ነው፡፡

እንዲሁም በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ትልቅ እድል የሚፈጥር መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ከዛሬ አንስቶ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

(via amn)

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

7 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.