በአዲስ አበባ ለሚገኙ የምህንድስና ተማሪዎች የተዘጋጀ የዲዛይን ውድድር ይፋ ተደረገ
በአዲስ አበባ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች የተዘጋጀ የመርካቶ አካባቢን መልሶ የማልማት የዲዛይን ውድድር ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
ውድድሩ በጣሊያን ንግድ ኤጀንሲ እና በጣሊያን ኤምባሲ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም እንደ ዩኒቲ ያሉ የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ያሳተፈ መሆኑ ተገልጿል ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህንፃ ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር ፋሲል ጊዮርጊስ ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት ውድድሩ ተማሪዎች በመርካቶ አካባቢ በሚገኝ ቦታ ላይ የዲዛይን ሀሳቦቻቸውን እንዲያቀርቡ እና እርስ በእርስ እንዲወዳደሩ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። አሸናፊ የሚሆነው ተማሪ ወደ ጣሊያን ሀገር በመሄድ ለአጭር ጊዜ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ አጭር የትምህርት እና የልምድ ልውውጥ እድል የሚያገኝ ይሆናል።
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ሀብታም ጌታቸው በበኩላቸው ውድድሩ ተማሪዎች ከከተማው ማህበራዊ እና ባህላዊ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣሙ አዲስ የዲዛይን ሀሳቦችን እንዲያመነጩ ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል። ውድድሩ በዘርፋ የሚሰማሩ ወጣት ተማሪዎች በከተማዋ ለውጥ ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እና ለፖሊሲ አውጪዎችም ጥሩ ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦችን ለማመንጨት ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል።
በሚኪያስ ፀሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል

8 hours ago