Logo
Getu Temesgen
በጅቡቲ አቅራቢያ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ቢያንስ 139 ስደተኞች ሕይወታቸው አለፈ
#ethiopia | የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳስታወቀው አደጋው የደረሰው በኦቦክ የዓሣ ማጥመጃ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ በምትገኘው ጉሄሬ አቅራቢያ ሲሆን ጀልባዋ 305 ስደተኞችን ጭና ከጅቡቲ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረችበት ሰጥማለች።

በአደጋው 84 ሰዎች አሁንም የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ የተረፉት 82 ሰዎች ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ዜጎች መሆናቸውን ድርጅቱ አረጋግጧል። IOM ይህንን ክስተት ከአፍሪካ ቀንድ ወደ ዓረብ አገራት በሚወስደው "ምሥራቃዊ የስደት መስመር" ላይ ከደረሱት እጅግ አሰቃቂ አደጋዎች አንዱ ሲል ገልጾታል።

የIOM የጅቡቲ ሚሲዮን ሃላፊ አሌክሳንደር ኮይሳክ "ይህ እጅግ የሚያስደነግጥ አደጋ ነው ሃሳባችን እና ጸሎታችን ከተረፉት እንዲሁም ወዳጆቻቸውን ካጡ እና ደብዛቸው ከጠፋባቸው ቤተሰቦች ጋር ነው" ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት IOM በኦቦክ በሚገኘው የስደተኞች ማዕከል ውስጥ ለ64 ተጎጂዎች የሕክምና፣ የምግብ እና የሥነ-ልቦና ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ የጅቡቲ ባለሥልጣናት ደግሞ የፍለጋ ሥራውን፣ የሕክምና እርዳታ እና የሟቾችን የቀብር ሥነ-ሥርዓት በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።

ይህ ምሥራቃዊ የስደት መስመር በዓለም ላይ ከሚበዙባቸው እና አደገኛ ከሆኑ የስደት ጎዳናዎች አንዱ ሲሆን በከባድ የበረሃ ሐሩር በእግር ከመጓዝ ጀምሮ በሕገ-ወጥ አሸጋጋሪዎች በታጨቁ አነስተኛ ጀልባዎች በቀይ ባህር እና በአደን ባህረ ሰላጤ ላይ በሚደረጉ አደገኛ ጉዞዎች የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ይበላል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.