Logo
Getu Temesgen
አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ምን አለ?
#ethiopia | የአሜሪካ ኤምባሲ በአስመራ/ኤርትራ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ውጊያ መቀጠሉን አስታውቋል።

በኤርትራ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች የጉዞ እገዳዎች፣ የፈንጂ ስጋቶች፣ የዘፈቀደ እስራት ስጋት እና የኤምባሲው የእርዳታ አቅም ውስን መሆን የተነሳ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል።

ኤርትራ የጣምራ ዜግነት ስለማትቀበል ኤርትራ -አሜሪካውያንን እንደ አንድ የኤርትራ ተራ ዜጋ ብቻ እንደምትቆጥራቸው ተገልጿል።

ግለሰቦች ግብር እንዲከፍሉ ሊገደዱ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ሊከለከሉ እና በብሔራዊ ግዳጅ ውስጥ እንዲሳተፉ ሊጠየቁ እንደሚችሉና በዚህም የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጥበቃ ሊያደርግላቸው እንደማይችል ተመላክቷል።

እንዲሁም ከአስመራ ውጭ ባሉ አካባቢዎች የኤምባሲ ሰራተኞች ከአስመራ ከተማ ማዕከል ከ25 ኪሎሜትር በላይ መጓዝ እንደማይችሉ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ አካባቢ ውጭ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት ያላቸው አቅም ውስን መሆኑ ተነግሯል።

ዜጎች በአሜሪካ መንግሥት እርዳታ ላይ የማይመረኮዝ የለቀቃ እቅድ እንዲያዘጋጁ፣ የጉዞ ሰነዶችን ወቅታዊና በቀላሉ ሊገኙ በሚችሉበት ሁኔታ እንዲይዙ፣ የዩናይትድ ስቴትት ፓስፖርት እና ወቅታዊ የኤርትራ ቪዛን ጨምሮ መታወቂያ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ ተጠይቀዋል።

በተጨማሪም የግል ደህንነት እቅዶችን በመገምገም የአካባቢን ዜናዎች እንዲከታተሉ እና በአስቸኳይ ጊዜ መረጃዎችን ለማግኘት በ Smart Traveler Enrollment Program (STEP) ላይ እንዲመዘገቡ አሳስቧል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

24 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.