Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
🕯️በጅቡቲ ባህር ዳርቻ እስካሁን በታወቀው የ139 ስደተኞች ህይወት አለፈ።

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነ አንድ ጀልባ ትናትንት ሌሊት ላዛሬ አጥቢያ  ሰጥሞ እስካሁን 139 ሰዎች መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (አይኦኤም) አሳወቀ።

ከሟቾቹ መካከል 15ቱ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል።

ከአደጋው 82 ሰዎች የተረፉ ሲሆን 84 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም።

ወደ የመን በመጓዝ ላይ የነበረውና 350 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር የሚገመተው ይህ ጀልባ፣ አደጋ የገጠመው በጅቡቲዋ ኦቦክ  አካባቢ ነው።  

ድርጅቱ እንደገለጸው፣ ድንበር ለማቋረጥ ከሚክሩት መካከል አብዛኞቹ ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ የሚመጡ ናቸው።

ከትላንት ለሊቱ አደጋ የተረፉት ከ80 በላይ ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተገልጿል።

እስካሁን ከተገኙት አስከሬኖች መካከል 52ቱ ወንዶች፣ 42ቱ ሴቶች ሲሆኑ 15ቱ ደግሞ ህጻናት ናቸው።

እስካሁን የት እንዳሉ የማይታወቁ 84 ሰዎች ያሉ ሲሆን የፍለጋና የነፍሥ ማዳን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ድርጅቱ አሳውቋል።

አይኦኤም እንደገለፀው በጎርጎሪያኑ 2025 ዓ/ም ይህንን ጉዞ ለማድረግ ሲሞክሩ ከ900 በላይ ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በጂቡቲ የሚገኘው የአይኦኤም የተልዕኮ ኃላፊ አሌክሳንደር ኮይሳክ አደጋውን " አውዳሚ " ሲሉ ጠርተውታል። 

" ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ስደተኞች የተሻለ የኢኮኖሚ እድል ለማግኘት በዚህ የፍልሰት መስመር ላይ የባብ ኤል-ማንዴብ ባሕረ ሰላጤ አቋርጠው ወደ የመን ለመድረስ  ሲሞክሩ የሚያጋጥሟቸውን አደጋዎች የሚያስታውስ ነው " ብለዋል።

ምንም እንኳ በመካከለኛው ምስራቅ አለመረጋጋት እየጨመረ ቢመጣም ድህነት፣ አለመረጋጋት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ብዙዎች ይህንን ጉዞ እንዲያያደርጉ እንዳስገደዳቸው ድርጅቱ ገልጿል።

የመን ውስጥ ከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ቢኖርም፣ ስደተኞች አሁንም ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ወደ የባህረ ሰላጤው አገራት ለመድረስ አስቸጋሪውን መንገድ እየተጓዙ ይገኛሉ።

በአይኦኤም የስደተኞች ክትትል መረጃ፣ ባለፈው አንድ ወር ብቻ ከ20,000 በላይ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የገቡ ስደተኞች ተመዝግበዋል።

#iom
ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.