#tigray
" ህወሓት ተመልሶ አይመጣም። .... የህወሓት አመራሮች ከኤርትራ ድንበር በስተደቡብ በኩል መረብ ወንዝ ዙሪያ ነው የሚገኙት " - አቶ ጌታቸው ረዳ
👉 " ወታደራዊ መልሶ ማጥቃት ለማድረግ ዝግጁ ነን ፤ የትኛውም ኃይል ከትግራይ አይወጣም " - ህወሓት
ለ6 ወራት ያህል ትግራይ በፌዴራል ኮማንድ ፖስት ስር እንደምትቆይና ከዚያ በኋላ ክልላዊ ምርጫ እንደሚካሄድ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።
አቶ ጌታቸው ከቲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ የኮማንድ ፖስቱ ዋነኛ ተግባር ክልሉን ለአስተዳደር ስራ ምቹ ማድረግ፣ ጸጥታን ማስከበር እንዲሁም መልሶ ማቋቋምና ማገገምን ማመቻቸት ነው።
እንደ አቶ ጌታቸው ማብራሪያ፣ የፌዴራል ኃይል እና አጋሮቹ እያንዳንዱን ከተማ ሲቆጣጠሩ ሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብ ሲሆን፣ የጸጥታ ጥበቃው በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) እና በትግራይ ሰላም ኃይል ይከናወናል።
በተጨማሪም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ6 ወር በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስር ለሚካሄደው ምርጫ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በወንጀል ድርጊት የተሳተፉት ካልሆኑ በስተቀር የህወሓት አባላት በትግራይ መልሶ ማቋቋም ስራ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ከቀናት በፊት ከኤርትራ ድንበር 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ዓዲግራት በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና በትግራይ ሰላም ኃይል ቁጥጥር ስር ውላለች።
አቶ ጌታቸው ረዳ ጦርነቱ ማብቃቱንና ህወሓት ተመልሶ የሚመጣበት እድል እንደሌለ ገልጸው፣ ዓድዋና አክሱም በቀጣይ ቀናት (ዛሬ ወይም ነገ) በቁጥጥር ስር እንደሚገቡ / እንደሚያዙ አመልክተዋል።
የህወሓት አመራሮች ከኤርትራ ድንበር በስተደቡብ በኩል መረብ ወንዝ ዙሪያ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ የህወሓት አመራር የሆኑት አማኑኤል አሰፋ እና የድርጅቱ ኮሙኒኬሽን በሶሻል ሚዲያ ባወጡት መግለጫ " ወታደራዊ መልሶ ማጥቃት ለማድረግ ዝግጁ ነን ፤ የትኛውም ኃይል ከትግራይ አይወጣም " ሲሉ አስታውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #mekelle📍 ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ለሁለት ሳምንት ያህል ተቋርጦ ዛሬ መልሶ በጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው በረራ፦ - አቶ ጌታቸው ረዳ - አብርሃም በላይ (ዶ/ር) - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥ ጀነራል ወዲ አንጥሩ - የትግራይ ሰላም ኃይል አመራር ሜጀር ጃነራል ዘውዱ ኪሮስ - ኮሎኔል ወዲ አባተ ... እንደነበሩበት ተነግሯል። የቀድሞው የትግራይ…

1 day ago