በትግራይ ክልላዊ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ፤ የፌደራል መንግስት “ሙሉ ትግራይን እንደሚያስተዳድር” አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ!
በትግራይ ክልል “ለምርጫ የሚሆን አመቺ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ” የፌደራል መንግስት “ሙሉ ትግራይን እንደሚያስተዳድር” የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። በክልሉ በፌደራል የሚመራ “ኮማንድ ፖስት” እንደሚቋቋም የገለጹት አቶ ጌታቸው፤ በሁሉም ቦታዎች በሚካሄድ ምርጫ የወረዳ አስተዳዳሪዎች እንደሚሰየሙ አስታውቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪነታቸው እንዲቀጥሉ በትላንትናው ዕለት በድጋሚ የተሾሙት አቶ ጌታቸው፤ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ቲቢኤስ ከተሰኘው የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
አንድ ሰዓት የሚጠጋ ጊዜ በወሰደው በዚህ ቃለ ምልልስ፤ አቶ ጌታቸው በትግራይ ክልል በቀጣይ የሚከናወኑ ስራዎችን በተመለከተም ጥቆማ ሰጥተዋል።
አቶ ጌታቸው ጥቆማውን የሰጡት ላለፉት ሳምንታት ሲካሄድ ከቆየ ውጊያ በኋላ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሚመሩ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩ የትግራይ ክልል በርካታ አካባቢዎች፤ በመከላከያ ሰራዊት እና አጋሮቹ መያዛቸውን ተከትሎ ነው።
የትግራይ ክልል አብዛኞቹ አካባቢዎች በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው፤ በክልሉ ከአሁን በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደማይኖር ይፋ አድርገዋል።
በፌደራል መንግስት እቅድ መሰረት በመጪዎቹ ስድስት ወራት በትግራይ ምርጫ ለማካሄድ እንደታቀደም አቶ ጌታቸው በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ገልጸዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube FikerAssefa

1 day ago