Logo
EBC
ማንቸስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐር 1 ለ 1 ተለያየ
*********************

በስድስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ቶተንሃም ሆትስፐርን ያሰተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ የውድድር ዓመቱን 3ኛ የአቻ ውጤት አስመዝግቧል።

የማንቸስተር ዩናይትድን ግብ ማቲያስ ኩኛ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ 72ኛው ደቂቃ ላይ ብሪያን እምቡሞ ከመረብ አሳርፏል።

ቤንትናኩርን 78ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጣው ቶተንሃም ነጥብ የተጋራበትን ግብ 90+2 ደቂቃ ላይ በዶሚኒክ ሶላንኬ አማካኝነት አስቆጥሯል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ብራይተንን ለቆ ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ካሜሩናዊው ካርሎስ ባሌባ ተቀይሮ ወደ ሜዳ በመግባት ለክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን ስድስት ያደረሰው ማንቸስተር ዩናይትድ 12ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ በውደድር ዓመቱ ለሦስተኛ ጊዜ አቻ የተለያየው ቶተንሃም ሆትስፐር በ3 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
#ebc #epl #premierleague #manchesterunited #tottenham #matchday EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.