ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው
*****************
የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ለፍትህ ሥርዓቱ መጠናከር በጋራ እንዲሠሩ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ጉባኤው ፍርድ ቤቶች በአደረጃጀታቸውና በሥልጣን ወሰናቸው ያደረጓቸውን እንቅስቃሴዎች በመፈተሽ ከስኬቶችና ከክፍተቶች ተሞክሮ ለመጋራት እንደሚያስችል አስታውቀዋል።
ተገልጋዮችን እርካታ የሚያረጋግጥ ተቀራራቢ የህግ አተረጓጎም እና አተገባበር እንዲኖር ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው፣ የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ ትርጓሜ ላይ በመቀናጀት የሚሠሩት አሠራር ድምበር የለሽ የሆነውን የፍትህ አገልግሎት ለማሳለጥ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዳኝነት አገልግሎት ዘርፍ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ሰብአዊ መብቶችንና ነፃነቶችን ለማስከበር እንዲሁም ለንግድና ኢንቨስትመንት መሳለጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህን ተልዕኮ ለማሳካት በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸው፣ ጉባኤው ለለውጥ ሥራው የላቀ ስኬት አስተዋጽኦ እንዳለው እምነታቸውን ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በራሔል ፍሬው
#ethiopia #ebc #justice #የመደመርመንግሥት #courtoffice

3 days ago