Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ ለ13ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1ሺ 102 ተማሪዎችን አስመረቀ

👉ኮሌጁ በ2020 ወደ ናሽናል ኤሮስፔስ ዩኒቨርስቲ ይሸጋገራል።

ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በዚህ ዓመት ከድህረ ምረቃ፣ ከመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ከሰርተፊኬት የሙያ ስልጠና ፕሮግራሞች በድምሩ 1ሺ 102 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባልና የናሽናል ኤርዌይስ እህት ኩባንያ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሰው ሀይል ልማት፣ በተለይም በአቪዬሽን፣ ቱሪዝም፣ ሆቴል፣ ሎጂስቲክስና ቢዝነስ ዘርፎች ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ ከአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA)፣ ከዓለም ኮሜርሻል ሜኔጅመንት (ICM) እና ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር  እየሰራ እንደሚገኝ ብስራት ሰምቷል።

ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት ወደ ናሽናል ኤሮስፔስ ዩኒቨርስቲ የመሸጋገር ሂደት ላይ ይገኛል። የናሽናል ኤሮስፔስ ዩኒቨርስቲ ራዕይ የተቋሙን አቅም ከአቪዬሽን ስልጠና አልፎ ወደ ኤሮስፔስ፣ የአየር እና የጠፈር ቴክኖሎጂ፣ ምርምር፣ ፈጠራ እና ከፍተኛ የሙያ ትምህርት የሚያስፋፋ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ሰላማዊ ነጋሲ

#ዳጉ_ጆርናል
3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.