Logo
Tikvah-University
#moe

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ለነበሩ ነባር ተማሪዎች ካደረገው ጊዜያዊ ምደባ ጋር በተያያዘ ለቀረቡ ቅሬታዎች የማጣራት ሥራ አጠናቆ ምላሽ ሰጥቷል።

በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ ለመመልከት 👇 https://student.ethernet.e...

የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሐግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሔድ ትምህርታችሁን መቀጠል እንደምትችሉ ተገልጿል።

በምደባው ላይ የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሔዳቹህ በፊት https://student.ethernet.e... ላይ በመግባት እንድታረጋግጡ ተብሏል።

አዲስ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ተቋም https://student.ethernet.e... ላይ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

🔔 ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ)ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
22 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.