Logo
Tikvah-University
#wallagauniversity

በ2019 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ2019 ትምህርት ዘመን ለሪሚዲያል ትምህርት ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡-
● በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ነቀምት ካምፓስ፣
● በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ስትማሩበት በነበረው ካምፓስ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

@tikvahuniversity
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.