Logo
EBC
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
****************

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፤ ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረና ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ውጤታማ ውይይቶች የሚካሄዱበት እንደሚሆን ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #india #diplomacy

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.