(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሊቢያ ቤንጋዚ አስተዳደር 100 ኢትዮጵያዊያንን ከአገር ማባረሩን አስታወቀ፡፡ የምስራቃዊ ሊቢያ ቤንጋዚ ባለስልጣናት በትላንትናው እለት 100 ያህል ኢትዮጵያዊያንን ማባረራቸውን አስታወቁ፡፡ የአገሪቱ ህገ ወጥ ስደትን የመከላከል ዳይሬክተር የታላቋ ቤንጋዚ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያዊያኑ የተባረሩት አስፈላጊውን ህጋዊ ሂደት ካጠናቀቁ በኋላ መሆኑን አስረድቷል፡፡
ይህ እርምጃ የተወሰደውም የዳይሬክሩ ሀላፊ ሜጀር ጄኔራል ሳላህ መሀመድ አል ካፊፊ ባወጡት መመሪያ መሰረት በሊቢያ የባህር ጠረፍ በኩል የሚደረገውን ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በቀጣይነትም በቤንጋዚ ውስጥ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች የመለየት ስራው እንደሚቀጥልና ሰነድ የሌላቸውን የማሰርና ከአገር የማባረር ዘመቻው እንደሚቀጥልም አስረድቷል፡፡
መግለጫው እነዚህን 100 ኢትዮጵያዊያን ከአገር ለማባረር የተጠቀመበትን መንገድ ወይንም መዳረሻቸው የት እንደሆነ ያለው ነገር የለም፡፡ ይህ መግለጫ የተሰጠው የምስራቃዊ ሊቢያ መንግስት የተለያዩ አገራት ዜጎች የሆኑ 258 ህገ ወጥ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ካስታወቀ ከቀናት በኋላ ነው፡፡

8 hours ago